ተቃዋሚዎች የሱዳን ዜና አገልግሎት ማዕከልን በተቃውሞ አናወጡ
የሱዳን የነጻነትና የለውጥ ኃይሎች ማዕከላዊ ምክር ቤት ሊሰጥ የነበረውን መግለጫ ለማስተጓጎል በማሰብ ነው ተቃዋሚዎቹ ወደ ማዕከሉ ያመሩት
ተቃዋሚዎቹ ወደ ማዕከሉ ለመግባት ሞክረው ነበር ተብሏል
የሱዳን የነጻነትና የለውጥ ኃይሎች ማዕከላዊ ምክር ቤት (Central Council of the Forces of the Declaration of Freedom and Change) ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 13 ቀን 2014 ዓ/ም ሊሰጥ የነበረውን ጋዜጣዊ መግለጫ የተቃወሙ ቡድኖች የሱዳን ዜና አገልግሎት ማዕከል በተቃውሞ አናወጡ፡፡
ተቃዋሚ ቡድኖቹ የሱዳን ዜና አገልግሎት (ሱና) ማዕከልን በተቃውሞ ያናወጡት የሱዳን የነጻነትና የለውጥ ኃይሎች ማዕከላዊ ምክር ቤት ሊሰጥ የነበረውን መግለጫ ለማስተጓጎል በማሰብ ነው ተብሏል፡፡
ተቃዋሚዎቹ ወደ ዜና አገልግሎቱ ቅጥር ግቢ በኃይል ለመግባት ሞከራ አድርገው ነበር የተባለ ሲሆን በማዕከሉ የእንግዳ መቀበያ ስፍራ ሲረብሹ እንደነበርም ተገልጿል፡፡
ሱዳን በአልፋሽቃ ከ142 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ የተዘራ ሰብል ሰበሰብኩ አለች
በዚህም ጋዜጣዊ መግለጫው ተሰርዞ ለሌላ ጊዜ መተላለፉን የዜና አገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሞሃመድ አብደል ሃሚድ አስታውቀዋል፡፡
ተቃዋሚዎቹ በሶስት ተሽከርካሪዎች ተጭነው ወደ ማዕከሉ መምጣታቸውን ያስታወቁት ዋና ዳይሬክተሩ አንድ ኮንቮይ በቤተ መንግስት አካባቢ ተቃውሞ ላይ የነበሩ ተጨማሪ 150 ሰዎችን ጭኖ ከዜና አገልግሎቱ ደጃፍ መድረሱን ተናግረዋል፡፡
“ ቡድኑ እንግዳ መቀበያው አካባቢ በኃይል ሲረብሽ ነበረ፤ እኛ ደግሞ በቂ ጠባቂዎች አልነበሩንምና ለፖሊስ ደውለናል” ሲሉም ነው ዋና ዳይሬክተሩ ያስቀመጡት፡፡
ሱዳን ከሰሞኑ በተከታታ ተቃውሞዎች በመናጥ ላይ ትገኛለች፡፡ ሃገራዊ ለውጡ እንዲመጣ ጉልህ አስተዋጽኦ በነበራቸው የነጻነትና የለውጥ ኃይሎች መካከል ልዩነት መፈጠሩ ሁኔታዎችን የበለጠ አባብሷል፡፡
የሱዳን ተቃዋሚዎች የቀድሞ አማጺዎችን ጭምር ያካተተ አዲስ ጥምረት መሰረቱ
በሲቪል እና ወታደራዊ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች መካከል የተካረረ ልዩነት መኖሩም ሁኔታውን የበለጠ እንዲከፋ አድርጎታል፡፡