የርገን ክሎፕ ሊቨርፑል ከአርሰናል በሚያደርገው ጨዋታ ላይ አንድም ደጋፊ እንዳይቀር አሉ
አርሰናል ለስድስት ቀናት ያለ ጨዋታ እንዲቆይ መደረጉ እንዳልገባቸው አሰልጣኝ ክሎፕ ተናግረዋል
በቅድሜው ጨዋታ ወደ አንፊልድ ሜዳ መምጣት የማይችሉ ደጋፊዎች ቲኬታቸውን መምጣት ለሚችሉ እንዲሰጡ ሲሉ አሰልጣኙ ጥሪ አቅርበዋል
የርገን ክሎፕ ሊቨርፑል ከአርሰናል በሚያደርገው ጨዋታ ላይ አንድም ደጋፊ እንዳይቀር አሉ።
18ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከዛሬ ጀምሮ መካሄድ የሚጀምር ሲሆን የፊታችን ቅዳሜ ምሽት 2:30 ጀምሮ ተጠባቂ ጨዋታ ይካሄዳል።
የፕሪሚየር ሊጉ መሪ አርሰናል ከሊቨርፑል የሚያደርጉት ጨዋታ በሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ሲሆን የሊቨርፑል አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ አስቀድመው ለደጋፊዎች ጥሪ አቅርበዋል።
ትናንት ምሽት በተካሄደ የካራባኦ ጨዋታ ዌስትሀምን 5 ለ 1 ያሸነፉት ሊቨርፑሎች በፕሪሚየር ሊጉ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
የሊጉን መሪነት ለመረከብ በሚደረገው በዚህ ተጠባቂ ጨዋታ አንድም የሊቨርፑል ደጋፊ ጨዋታው ወደሚካሄድበት አንፊልድ እንዳይቀር ተብለዋል።
አሰልጣኙ አክለውም በተለያዩ ምክንያቶች ወደ አንፊልድ መምጣት ያልቻለ ደጋፊ ቲኬታቸውን መምጣት ለሚችሉ ደጋፊዎች እንዲሰጡ ሲሉም ተናግረዋል።
አሰልጣኙ ለደጋፊዎች ጥሪ ያቀረቡት ባሳለፍነው እሁድ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር በተካሄደው እና በአቻ ውጤት በተጠናቀቀው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ አንፊልድ ቀዝቅዟል የሚል ትችት መሰንዘሩን ተከትሎ ነው።
በዛሬው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ክሪስታል ፓላስ ከብራይተን የሚጫወቱ ሲሆን በነገው ዕለት ደግሞ አስተን ቪላ ከሼፊልድ ዩናይትድ ይጫወታሉ ተብሏል።
አርሰናል ፕሪሚየር ሊጉን በ39 ነጥብ እየመራ ሲሆን ሊቨርፑል እና አስተን ቪላ ደግሞ በግብ ተበላልጠው ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃዎችን ይዘዋል።
አስተን ቪላ በነገው ጨዋታ ሼፊልድ ዩናይትድን የሚያሸንፍ ከሆነ ሊጉን በ41 ነጥቦች መምራት የሚጀምር ይሆናል።