በቱርክ የክለብ ፕሬዝደንት ዳኛ መምታቱን ተከትሎ ሁሉም የእግር ኳስ ውድድሮች ታገዱ
ክለቡ ለተፈጠረው ድርጊት የቱርክን እግርኳስ ማህበረሰብ ይቅርታ ጠይቋል
ሀሊል ኡመት ሜለር የተባለው ዳኛ በኤምኬኢ አንካራጉሱ ክለብ ፕሬዝደንት ፋሩክ ኮካ ፊቱ ላይ በቦክስ ተመትቶ ወድቋል
በቱርክ የክለብ ፕሬዝደንት ዳኛ መምታቱን ተከትሎ ሁሉም የእግር ኳስ ውድድሮች ታገዱ።
በከፍተኛ ሊግ ጨዋታ መጨረሻ ላይ የክለብ ፕሬዝደንት ታዋቂ ዳኛን መትቶ ከመሬት መጣሉን ተከትሎ በቱርክ የሚካሄዱ ሁሉም ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ውድድሮች ታግደዋል።
ሀሊል ኡመት ሜለር የተባለው ዳኛ በኤምኬኢ አንካራጉሱ ክለብ ፕሬዝደንት ፋሩክ ኮካ ፊቱ ላይ በቦክስ ተመትቶ መውደቁን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
በቦታው የነበሩ ተመልካቶች ግማሾቹ ለመገላገል ሙከራ ሲያደርጉ ሌሎች ደግም ከፍተኛ ጩኸት ሲያሰሙ ነበር ተብሏል።
መሬት የወደቀው ሜለር ጭንቅላቱ ላይ አንድ ጊዜ ተመትቷል።
ሜለር ድብደባ ያጋጠመው የመራው የኤምኬኢ አንካራጉሱ እና የተቀናቃኙ ሪዘስፖር የከፍተኛ ሊግ ጨዋታ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ከተጠናቀቀ በኋላ ነው።
የቱርክ እግርኳስ ፌደሬሽን (ቲኤፍኤፍ) ድርጊቱን አውግዞ ሁሉም ውድድሮች ላልተወሰነ ጊዜ ታግደው እንዲቆዩ የወሰነ ሲሆን የቱርኩ ፕሬዝደንት ኢርዶጋን ደግሞ ሰፖርት "የሰላም እና የወንድማማችነት ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
በቱርክ ዳኛ የደበደቡት የክለብ ፕሬዝደንት
— Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ (@AlainAmharic) December 12, 2023
ሀሊል ኡመት ሜለር የተባለው ዳኛ በኤምኬኢ አንካራጉሱ ክለብ ፕሬዝደንት ፋሩክ ኮካ ፊቱ ላይ በቦክስ ተመትቶ መውደቁን ተዘግቧል።https://t.co/9pohlJKaFj pic.twitter.com/ys5HRDZ5jU
ቲኤፍኤፍ ባወጣው መግለጫ ጥቃቱ የተጨዋቾች እና የክለብ ባለስልጣናት በዳኞች ላይ ለአመታት ባዳበሩት መጥሮ ባህል ምክንያት የመጣ ነው ብሏል።
ቲኤፍኤፍ እንደገለጸው በፕሬዝደንቶች፣ በማናጀሮች፣በክለቦች፣ በተጨዋቾች እና በአሰልጣኞች እና የቲቪ ኮሜንታተሮች በዳኞች ላይ ሲያቀርቡት የነበረው ተገቢ ያልሆነ አስተያየት እንዲህ አይነት ጥቃት እንዲከፈት መንገድ ከፍቷል።
ድርጊቱን የፈጸሙትን ተጠያቂ ለማድረግ ምርመራ መጀመሩን ቲኤፍኤፍ ገልጿል።
ቲኤፍኤፍ "ተጠያቂው ክለብ፣ ፕሬዝደንቱ፣ ማናጀሩ እና ሁሉም ወንጀለኞች አስፈለጊውን ቅጣት ያገኛሉ" ብሏል።
ሜለር እና ኮካ ሁለቱም ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን እና ኮካ ሊታስር እንደሚችል እና እየተጠበቀ መሆኑን የቱርክ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
ኤምኬኢ አንካራጉሱ ክለብ በኤክስ ገጹ ላይ "እንደ ኤምኬኢ አንካራጉሱ ስፖርት ክለብ በተፈጠረው ክስተት አዝነናል" ብሏል።
ክለቡ ለተፈጠረው ድርጊት የቱርክን እግርኳስ ማህበረሰብ ይቅርታ ጠይቋል።