ኢኮኖሚ
ትናንት ከተጀመረው የአለም ኢኮኖሚ ፎረም ጋር የማንቸስተር እግር ኳስ ክለብ ስም ለምን ተነሳ?
ጉባኤው የፈረንጆች 2023 ለንግድና ለመንግስታት ፈተና ይሆናሉ በተባለበት ጊዜ መካሄዱ ወጤቱን ተጠባባቂ አድርጎታል
ማንቸስተር ዩናይትድ በዳቮስ ጎዳናዎች እንግዳ መቀበሉን ተከትሎ ክለቡ ገዥ እያፈላለገ ነው ተብሏል
የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ከሦስት ዓመታት በኋላ ወደ ዳቮስ ተመልሷል።
በታዋቂው ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የመንግስት ባለስልጣናት እና የንግድ መሪዎች ይጠበቃሉ።
ነገር ግን በፈረንጆች 2023 ለንግድና ለመንግስታት ፈተና መሆኑን የሚያስጠነቅቁ ሁለት ጥናቶች የስዊሷን ከተማ የመጪው የኢኮኖሚ ድቀት ጥላ አጥልቶባታል። የዳቮስ ታዳሚዎች ለሮይተርስ እንደተናገሩት ጥቂት ዘርፎች ከሚመጣው ማዕበል ይከላከላሉ ብለው ይጠብቃሉ።
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ እየተከሰተ ያለውን የኃይል ችግር ለመቅረፍ ሀገራቸው መቆየትን መርጠዋል።
ስዊዲናዊት የአየር ንብረት ተሟጋች ግሬታ ቱንበርግ በዳቮስ መገኘት አለመገኘት የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል።
የእግር ኳስ ክለቡ ማንቸስተር ዩናይትድ በዳቮስ ጎዳና ላይ በሩን ክፍት ያደርጋልም ተብሏል። ነገር ግን ክለቡ ገዥዎችን ከመሳብ ይልቅ ደንበኞችን እና አጋሮችን ለማዝናናት መሆኑን አስረግጦ ተናግሯል።
ባለፈው ህዳር ክለቡ ከ17 ዓመታት በኋላ አዲስ ኢንቨስትመንት ለማግኘት ወይም ሊሸጥ የሚችልበትን አማራጭ እየፈለገ መሆኑን ተናግሯል።