ስለማንችስተር ዩናይትድ እና አርሰናል ወቅታዊ አሀዛዊ መረጃዎች ምን ይነግራሉ?
ዩናይትድ ባለፉት ጊዜያት ከሜዳው ውጭ ከአርሰናል ጋር ካደረጋቸው 9 ጨዋታዎች ሰባቱን ተሸንፏል
አርሰናል በሁሉም የሊግ ጨዋታዎች በኤሜሬትስ 500ኛ ጨዋታውን ዛሬ ያደርጋል
ተቀናቃኝ የእንግሊዝ ቡድኖች ማንችስተር ዩናይትድ እና አርሰናል ለ242ኛ ጊዜ ዛሬ ምሽት 5፡15 ላይ በአሜሬትስ ስታድየም ይገናኛሉ፡፡
አርሰናል በዛሬው ምሽት ጨዋታ የሚያሸነፍ ከሆነ በሊጉ ከመሪው ጋር ያለውን ልዩነት ለማጥበብ የሚያግዘው ሲሆን በተጨማሪም በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በዩናይትድ ላይ ተከታታይ አራት ጨዋታዎችን ድል በመቀዳጀት ታሪክ የሚጽፍበት ነው፡፡
ከዚህ ቀደም በተደረጉ 241 ግጥሚያዎች መድፈኞቹ 89 ጊዜ ሲያሸንፉ ቀያይ ሰይጣኖቹ በ10 ጨዋታ ልቀው 99 ጨዋታዎችን በድል ተወጥተዋል፤ 53 ግጥሚያዎች ደግሞ በአቻ የተለያዩባቸው ናቸው፡፡
ስለ ማንችስተር ዩናይትድ እና አርሰናል ወቅታዊ አሃዛዊ መረጃዎች ምን ይነግራሉ?
አርሰናል
-አርሰናል በሁሉም የሊግ ጨዋታዎች በኤሜሬትስ 500ኛ ጨዋታውን ዛሬ ምሽት ያከናውናል
-የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ በዘንድሮው የውድድር አመት ለመጀመርያ ጊዜ ሶስት ጨዋታዎችን በተከታታይ ማሸነፉን ያረጋግጣል።
-በሊጉ እስከ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኙ ቡድኖች ጋር ያደረጋቸውን 15 ጨዋታዎች አልተሸነፈም።
-መድፈኞቹ ባለፉት 11 ጨዋታዎች 8 ጎሎችን ያስቆጠሩት በመጀመርያ አጋማሽ ነው
-አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አርሰናልን ከተረከበ ጀምሮ ከማንችስተር ጋር ከተደረጉ 9 ጨዋታዎች ስድስቱን በአሸናፊነት አጠናቋል
-በፕሪምየር ሊጉ ቢያንስ አምስት ጊዜ ቀያይ ሰይጣኖቹን ከገጠሙ አሰልጣኞች መካከል አርቴታ በ67 በመቶ ከፍተኛ የማሸነፍ እድል አለው
-ወጣቱ አጥቂ ቡካዮ ሳካ በዩናይትድ ላይ ሶስት ግቦችን ሲያስቆጥር 2 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል፤ በዚህም በዩናይትድ ላይ በተቆጠሩ 12 ጎሎች ላይ ተሳትፎ ከነበረው ቲየሪ ሄንሪ በመከተል ሁለተኛው የአርሰናል ተጫዋች ነው
-ሳካ እና ካይ ሃቨርት በጋራ 10 ጎሎችን በማስቆጠር የዘንድሮው የውድድር አመት የክለቡ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሲሆኑ ከ10 ጎሎች ስምንቱን ያስቆጠሩት በኤምሬትስ ስታዲየም ነው
-ካለፈው የውድድር ዘመን ጀምሮ አርሰናል ያስቆጠራቸው 20 ጎሎች ከማዕዘን የተሻሙ ናቸው
ማንቸስተር ዩናይትድ
-ዩናይትድ ባለፉት ጊዜያት ከሜዳው ውጭ ከአርሰናል ጋር ካደረጋቸው 9 ጨዋታዎች ሰባቱን ተሸንፏል
-በሳምንቱ አጋማሽ ባደረጋቸው ያለፉት ሰባት የሊግ ጨዋታዎች ስድስቱን በማሸነፍ በአጠቃላይ 38 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።
-በለንደን ካደረጓቸው 18 የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ሁለቱን ብቻ ሲያሸንፉ ሁለቱም ድሎች በፉልሃም ላይ የተቀዳጇቸው ናቸው
-ለመጨረሻ ጊዜ ባደረጓቸው አምስት ጨዋታዎች 4 ሲያሸንፉ አንድ አቻ ወጥተዋል
-በአምስት ጨዋታዎች የነበራቸው የጎል ምጣኔ 40.0 በመቶ ሲሆን የማሸነፍ ምጣኔያቸው ደግሞ 80 በመቶ ደርሷል
-ካለፉት 4 የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች 8 ነጥቦችን በመሰብሰብ ደረጃቸውን ወደ 9 ከፍ አድርገዋል
-በደረጃው በሁለተኛነት ከሚገኝው አርሰናል ጋር ያላቸው የነጥብ ልዩነት 6 ብቻ ነው
-ዩናይትድ ባስቆጠራቸውን ሰባት የፕሪሚየር ሊግ ግቦች አማድ ዲያሎ አራት ብሩኖ ፈርናንዴዝ ደግሞ 3 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችተው አቀብለዋል
-ማርከስ ራሽፎርድ በሩበን አሞሪም ስር ባደረጋቸው ሁለት የሊግ ጨዋታዎች ሶስት ጎሎችን አስቆጥሯል
የምሽቱ ጨዋታ በብዙ መለኪያዎች ለሁለቱም ቡድኖች ወሳኝነቱ ከፍ ያለ ነው፤ ኤቨርተንን 4 ለ0 አሸነፎ ደረጃውን ወደ 9 ከፍ ያደረገው ዩናይትድ የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ በ22 ነጥብ ቶፕ 6 ውስጥ መግባት ይችላል፡፡
መድፈኞቹ በበኩላቸው በሊጉ በአሸናፊነት ግስጋሴ እየቀጠለ ከሚገኝው መሪው ሊቨርፑል ጋር ያላቸውን የ9 ነጥብ ልዩነት የዛሬውን ጨዋታ በማሸነፍ ወደ 6 ዝቅ ማድረግ ይፈልጋሉ፤ ይህም ለዋንጫ ፉክክር ያላቸውን እድል የሚያለመልም ይሆናል፡፡