በአውሮፓው ድርቅ የውሃ መጠን በመቀነሱ በ2ኛው የአለምጦርነት ወቅት የነበሩ የጦር መርከቦች ብቅ አሉ
የውሃ መጠኑ ዝቅ ማለት ባህር ሰርጓጅ የሆኑ ቅርሶችና ያልተፈለጉ ነገሮች ለእይታ እንዲጋለጡ አድርጓል፡፡
በስፔን አርኪኦሎጂስቶች የስፔን የድንጋይ አጥር በመባል የሚታወቁት በውሃ ተሸፍነው የነበሩት የቅድመ ታሪክ ድንጋዮች መገኘታቸው አስደስቷቸዋል
በአውሮፓ በተከሰተው ድርቅ ምክንት የውሃ መጠን በመቀነሱ የጥንት ድንጋዮች እና በ2ኛው የአለም ጦርነት ወቅት የነበሩ የጦር መርከቦች ብቅ ሊሉ ችለዋል፡፡
በአውሮፓ በተከሰተው ነዳድ ድርቅ ምክንያት ወንዞች እና ኃይቆች ጥቂቶች መስታወስ እስከሚችሉት ድረስ ዝግ ማለቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡የውሃ መጠኑ ዝቅ ማለት ባህር ሰርጓጅ የሆኑ ቅርሶችና ያልተፈለጉ ነገሮች ለእይታ እንዲጋለጡ አድርጓል፡፡
በከፍተኛ ድርቅ እየተሰቃየች ባለችው ስፔን፤ አርኪኦሎጂስቶች የስፔን የድንጋይ አጥር በመባል የሚታወቁት በውሃ ተሸፍነው የነበሩት የቅድመ ታሪክ ድንጋዮች መገኘታቸው አስደስቷቸዋል ሲል ዘገባው ጠቅሷል፡፡
በመደበኛ ስያሜያቸው ዶምሌን ኦፍ ጓደልፔራል የሚባሉት ድንጋዮች የስፔን ባለስልጣናት የወሃ መጠን በ28 በመቶ ቀንሷል በሚባለው ካሴርስ ማእከላዊ ግዛት በሚገኘው ግድብ አንድ ጫፍ ተጋልጠውይገኛሉ፡፡
ቦታው በፈረንጆቹ በ1926 በጀርመናዊ ጂኦሎጂስት ሁጎ ኦበርሜር የተገኘ ሲሆን በ1963 በሰፔኑ ፋራንሲስኮ የገጠር ልማት ፕሮጀክት ጊዜ በጎርፍ ተወስዶ ነበር፡፡
ከዚያን ጊዜ ወዲህ በትክክል የታየው አራት ጊዜ ብቻ ነው፡፡
በውሃ መጠን መቀነስ ምክንያት በጀመርንም ባሉ ወንዞች የ”ረሃብ ድንጋይ” የሚባለው በራይን ወንዝ ተገኝቷል፡፡