የዊኪሊክስ መስራቹ አሳንጅ ከፍትህ ይልቅ ነጻነትን መምረጡን ተናገረ
አሳንጅ የስዊድን ባለስጣናት በወሲብ ጥቃት ጠርጥረው እንደሚፈልጉት ከገለጹ በኋላ ነበር በአውሮፓ የእሰር መያዣ ትዕዛዝ በ2010 በእንግሊዝ የታሰረው።
አሳንጅ ህጋዊ እና ፖለቲካዊ ጥረቶች ነጻቱን ለማስጠበቅ ዋስትና ስለሌላቸው በቀረበበት የአሜሪካ የስለላ ክስ ጥፋተኛ እንደሆነ ማመኑ ተናግሯል
የዊኪሊክስ መስራቹ አሳንጅ ከፍትህ ይልቅ ነጻነትን መምረጡን ተናገረ።
አሜሪካ ሚስጥራዊ መረጃዎችን በመስረቅ የከሰሰችው ጁሊን አሳንጅ ከእስር ከተፈታ በኋላ በሰጠው የመጀመሪያ ይፋዊ አስተያየት ከፍትህ ይልቅ ነጻነትን መርጦ እንደነበር ተናግሯል።
ዊክሊክስ የተባለው የሚዲያ ቡድን መስራች የነበረው አሳንጅ ህጋዊ እና ፖለቲካዊ ጥረቶች ነጻቱን ለማስጠበቅ ዋስትና ስለሌላቸው በቀረበበት የአሜሪካ የስለላ ክስ ጥፋተኛ እንደሆነ ማመኑ አስፈላጊ መሆኑን ለአውሮፓ ህግ አውጭዎች በዛሬው እለት ተናግሯል።
አሳንጅ ከእስር ከተፈታ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጠው መግለጫ "በመጨረሻም ሊሳካ ከማይችል ፍትህ ይልቅ ነጻነትን መርጫለሁ" ብሏል።
የ53 አመቱ አሳንጅ ከ14 አመታት የእንግሊዝ የህግ ክርክር በኋላ ወደ ትውልድ ሀገሩ ባለፈው አውስትራሊያ ባለፈው ሐምሌ የተመለሰው ከአሜሪካ በደተረገ ስምምነት ነው። በስምምነቱ መሰረት አሳንጅ የአሜሪካን የስለላ ህግ በመጣስ ጥፋተኛ ነኝ ብሎ ሲያምን ተላልፎ እንዲሰጣት ስትጠይቅ የነበረችው አሜሪካ ደግሞ አሳንጅ ተፈትቶ ወደ አውስትራሊያ እንዲሄድ ፈቅዳለች።
ዊኪሊክስ በ2010 ዋሽንግተን በአፍጋኒስታን እና በኢራቅ ያደረገቻቸውን ጦርነቶች የሚያሳዩ በ100ሺዎች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ወታደራዊ ሚስጥሮችን ይፋ አድርጎ ነበር። ይህ በአሜሪካ ወታደራዊ ታሪክ እጅግ ከፍተኛ የሚባል ጥሰት መሆኑም ተገልጾ ነበር።
አሳንጅ ከአንድ አመት በኋላ በአሜሪካ የስላላ አዋጅ መሰረት ክስ ተመሰረተበት።
የአውሮፓ ካውንስል የፓርላማ ጉባኤ ያወጣው የመጀመሪያ ሪፖርት አሳንጅ የፖለቲካ እስረኛ መሆኑን መደምደሙን እና ኢሰብአዊ አያያዝ ተፈጽሞበት ከሆነ ማጣራት እንዲደረግ ለእንግሊዝ መንግስት ጥሪ አቅርቦ ነበር።
ከባለቤቱ ስቴላ እና ከዊኪሊክስ ኢዲተር ክርስቲን ህራፍሰን ጎን ተቀምጦ በሰጠው መግለጫ "ስላሳለፍኩት መከራ ለመናገር ገና ነኝ" ብሏል።
አሳንጅ አክሎም "በብቸኝነት ያሳለፉኩት ጊዜ ያሳደረብኝን ተጽዕኖ ለማስወገድ እየመከርኩ ነው" ሲል ተናግሯል።
አሳንጅ በገባው የጥፋተኝነት ስምምነት መሰረት ከአሜሪካ የስላላ ክስ ራሱን እንዳይከላከል ታግዷል።
"ስለሆነው ነገር ድጋሚ ክርክር አይኖርም" ብሏል።
ባለፈው ወር በለንደን እስርቤት ሆኖ ያገባት የአሳንጅ ሚስት ጤናውን ለማግኘት ጊዜ እንደሚፈልግ ተናግራ ነበር።
ቀጣይ እቅዱ ምን እንደሆነ የተጠየቀው አሳንጅ የመረጃ አነፍናፈዎችን እና ጠቋሚዎችን በመጠበቅ ዙሪያ ግንዛቤ ማዳበር "የመጀመሪያ እርምጃው" እንደሆነ ገልጿል።
አሳንጅ የስዊድን ባለስጣናት በወሲብ ጥቃት ጠርጥረው እንደሚፈልጉት ከገለጹ በኋላ ነበር በአውሮፓ የእሰር መያዣ ትዕዛዝ በ2010 በእንግሊዝ የታሰረው።
አሳንጅ በስዊድን የቀረበበትን ክስ በመሸሽ ለሰባት አመታት ያህል በእንግሊዝ በሚገኘው የኢኳዶር ኢምባሲ ውስጥ ቆይቷል። ስዊድን ቆይታ ክሱን አንስታዋለች።
በ2019 ከኢምባሲው እንዲወጣ ተደርጎ እስከሚፈታበት ድረስ ከፍተኛ ጥበቃ ወደሚደረግበት የለንደኑ ቤልማርሽ እስርቤት መዛወሩ ይታወሳል።