የብሪታኒያ ፍርድ ቤት የዊኪሊክስ መስራች ዊሊያም አሳንጅ ለአሜሪካ ተላልፎ እንዲሰጥ ወሰነ
የብሪታኒያ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ካፀደቀ አሳንጅ ለአሜሪካ ተላልፎ ይሰጣል
አውስትራሊዊው አሳንጄ መረጃ በመበርበርና በመሰለል ወንጀል ከተከሰሰ 10 ዓመታት አልፈዋል
በአሜሪካ በጥብቅ የሚፈለገው የዊኪሊክሱ መስራች ጁሊያን አሳንጅ ለአሜሪካ ተላፎ እንዲሰጥ የብሪታኒያ ፍርድ ቤት ወሰነ።
አሳንጅ ለአሜሪካ ፍርድ ቤት ተላልፎ እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱ ያሳለፈው ውሳኔ ተፈጻሚ የሚሆነው የብሪታኒያ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ሲያጸድቀው ነው ተብሏል።
የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሯ ፍርድ ቤቱ የወሰነውን ውሳኔ በመከተል አሳንጅን ወደ አሜሪካ ያዘዋውሩታል ወይስ አያዘዋውሩትም የሚለው በቀጣይ የሚታይ ይሆናል ተብሏል።
ይሁንና ፍርድ ቤቱ አሳጄ ወደ አሜሪካ እንዲዘዋወር መወሰኑ የግለሰቡን ወደ አሜሪካ መሄድ በአንድ ደረጃ ከፍ እንዳደረገውም ተነግሯል።
የአሳንጅ ፍርድ በሚታይበት ለንደን ፍርድ ቤት አካባቢ በርካታ ደጋፊዎቹ ተሰባስበው እንደነበር ተሰምቷል። አውስትራሊዊው አሳንጅ መረጃ በመበርበርና በመሰለል ወንጀል ከተከሰሰ 10 ዓመታት አልፈዋል።
ዛሬ የተወሰውን ውሳኔ የመጨረሻ ብይን የሚሰጠው የብሪታኒያ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ሲሆን፤ የተቋሙ ውሳኔም እየተጠበቀ እንደሆነ ተገልጿል።
የአሜሪካን ወታደራዊ መረጃዎች በማነፍነፍና በማተም እንዲሁም ወታደራዊ ሚስጥሮች የያዙ ሰነዶች ለውጭ ኃይሎች አሳለፎ ሰጥቷል በሚል በአሜሪካ ባለስልጠናት በኩል ጥርስ የተነከሰበትና 18 በሚሆኑ ክሶች ዋና ተፈላጊ ሰው መሆኑ ይታወቃል።
ምንም እንኳ የ50 ዓመቱ አሳንጅ በአሜሪካ የቀረበለትን ክስ ውድቅ ቢያደረግም፤ አድርጎታል ከተባለ ድርጊት ጋር በተያያዘ ለ7 ዓመታት በለንደን በሚገኘው የኢኳዶር ኤምባሲ፤ እንዲሁም እንደፈረንጆቹ ከ2019 አንስቶ አስካሁን ድረስ በደቡብ ምስራቅ ለንደን በሚገኘው የቤልማርሽ እስር ቤት እንዲታሰር ምክንያት ሆኖታል።