አርሰናል የሪያል ማድሪዱ ማርኮ አሴንሲዮን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምሯል ተባለ
ከአርሰናል በተጨማሪ ቼልሲ እና ማንቸስተር ሲቲ የተጫዋቹ ፈላጊዎች ናቸው
አሴንሲዮ የክርስቲያኖ ሮናልዶ ተተኪ ሊሆን እንደሚችል ተስፋ ቢጣልበትም እስካሁን አልተሳካለትም
አርሰናል የሪያል ማድሪዱ ማርኮ አሴንሲዮን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምሯል ተባለ።
የእንግሊዙ ክለብ አርሰናል የ27 አመቱን የማድሪድ ኮከብ ማርኮ አሴንሲዮን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምሯል ተባለ፡፡
ቲም ቶክ እንደዘገበው አርሰናል ከሪያል ማድሪድ ጋር ያለውን ኮንትራት በቅረቡ የሚያጠናቅቀው ማርኮ አሴንሲዮ ለማስፈረም ጥያቄ ሊያቀርብ ነው።
ስፔናዊው የፊት መስመር አጥቂ በክረምቱ ቤርናባውን በነጻ ዝውውር በመልቀቅ ወደ ፕሪምየር ሊግ ሊቀላቀል እንደሚችልም ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት፡፡
ከአርሰናል በተጨማሪ ቼልሲ እና ማንቸስተር ሲቲ የተጫዋቹ ፈላጊዎች መሆናቸው ታውቀዋል፡፡
ይሁን እንጅ ስፔናዊው ኮከብ አርሰናል መቀላቀሉ እድል ከፍተኛ እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡
ምክንያቱም ደግሞ መድፈኞቹ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እንደ ማርቲን ኦዴጋርድ እና ዳኒ ሴባልሎስን ለመግዛት ስምምነቶች ካደረጉ በኋላ ከሪያል ማድሪድ ጋር ጥሩ የስራ ግንኙነት አላቸው።
የ 27 አመቱ ተጫዋች በበርናባው የክርስትኖ ሮናልዶ ይተካል ተብሎ ነበረ ቢሆንም የተጠበቀው ያህል እንዳልሆነ ይነሳል፡፡
አሴንሲዮ መድፈኞችን የሚቀላቀል ከሆነ ቡካዮ ሳካን በመተከታም ሆነ በአጥቂው አማካይ ቦታ ላይ ተጨማሪ ጥንካሬ በመፍጠር ረገድ ትልቅ ሚና የሚኖረው ይሆናል፡፡
እናም የተጫዋቹ ፈላጊዎች ማንቸስተር ሲቲ እና ቼልሲ ከመቅደማቸው በፊት አርሰናል መቅደም ይጠበቅባቸዋል፡፡
የአሴንሲዮም የቀድሞ የማድሪድ ጓደኛና የመድፈኞቹ አምበልነት ኦዴጋርድ ተጫዋቹ ወደ አርሰናል እንዲገባ ሊያግባበው ይችላልም እየተባለ ነው፡፡