በዴሞክራሲያዊ ኮንጎ በተጠርጣሪ ኤዲኤፍ ታጣቂዎች በትንሹ 21 ሰዎች ተገደሉ
ባለፈው አመት በፈረንጆቹ ጥር ወር 25 ንጹኃን መገደቸውን ዘገባው አስረድቷል
የተመድ ሰብአዊ መብት ቢሮ ባለፈው አመት ባቀረበው ሪፖርት መሰረት ኤዲኤፍ የጦር ወንጅል መፈጸሙን ገልጿል
በምስራቃዊ ዴሞክራሲያዊ ኮንጎ (ዲአር ኮንጎ) በተጠረጠሩ የጥምር ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች (ኤዲኤፍ) በትንሹ 21 ንጹሃን መገደላቸውን ሲጂቲኤን የአካባቢውንና የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን (ተመድ) ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
ጥቃቱ የተከሰተው ከሪዎንዞሪ ዋና ከተማ ከሆነችው ሙትዋንጋ ከተማ በ9ኪሎሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው ምዌንዳ መንደር ነው፡፡
ሲጂቲኤን ከተመድ የሰላም አስከባሪ ሚሽን አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት የሟቾች ቁጥር 21 መሆኑን የገለጸ ሲሆን የቤኒ ከተማ አስተዳዳሪ የሆኑት ዶናት ኪብዋና በበኩሉ የሟቾችን ቁጥር 22 ነው ብሏል፤ ከሟቾቹ 10ሩ ሴቶች መሆናቸውንም አስታውቋል፡፡
አስተዳዳሪው እንዳሉት ሌሎች 10 ሰዎች መቁሰላቸውንና ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች መጎዳታቸውንም ተናግረዋል፡፡በአካባቢው ያለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ፓሉኩ እንዳሉት ደግሞ ጥቃት መከሰቱን ያረጋገጡ ሲሆን በቢሮቸው ላይም ጉዳት መድረሱን አስታውቀዋል፡፡
ይህ ጥቃት በአካባቢው ከተከሰቱት ጥቃቶች የቅርብ ጊዜ የሚባል ነው፤ባለፈው አመት በፈረንጆቹ ጥር ወር 25 ንጹኃን መገደቸውን ዘገባው አስረድቷል፡፡
በኡጋንዳ የተቋቋመው ኤዲኤፍ ከእስላማዊ መንግስት ጋር ግንኙት እንዳለው መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በፈረንጆቹ 2019 መጨረሻ አካባቢ የኮንጎ ጦር በምስራቃዊ የሀገሪቷ ክፍል በሚገኙ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ወስዶ ነበር፤ነገርግን ይህ ጥቃት ታጣቂዎቹ የበቀል እርምጃ እንዲወስዱ አድርጓቸዋል፡፡
የተመድ ሰብአዊ መብት ቢሮ እንዳስታወቀው ባለፈው አመት ባቀረበው ሪፖርት መሰረት ኤዲኤፍ የጦር ወንጀል መፈጸሙን ገልጿል፡፡