ልዩልዩ
ጋና በኮቪድ ምክንያት ለዘጠኝ ወራት ተዘግተው የቆዩ ት/ቤቶችን ልትከፍት ነው
በጋና እስካሁን ከ55ሺ በላይ ሰዎች በኮሮና የተያዙ ሲሆን 335 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል
በጋና ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱት ከተዘጉ ከ9 ወራት በኋላ መሆኑ ተገልጿል
በጋና ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት በኋላ ለ9 ወራት ተዘግተው የነበሩት ትምህርት ቤቶች በዚህ ወር መከፈታቸውን የጋናው ፕሬዘዳንት ናና አኩፎ አዶ ገልጸዋል፡፡
ፕሬዘዳንቱ በኮቪድ ላይ ስለወሰዱት እርምጃ በተናገሩበት ወቅት እንዳስታወቁት ቅድመ መደበኛ፣የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በፈረንጆቹ ጥር 15 የሚከፈቱ ሲሆን ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በፈረንጆቹ ጥር 18 አንዲሁም ከፍተኛ ትምህርት ደግሞ በፈረንጆቹ ጥር 9 ይከፈታሉ፡፡
ባለፈው አመት እንዳንድ የትምህርት ተቋማትን በመክፈት ልምድ ተገኝቷል ያሉት ፕሬዘዳንቱ ይህም ሙሉ በሙሉ ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት አስችሎናል ብለዋል፡፡ የጥንቃቄ ጉዳይ እንዳለ ቢሆንም ልጆች ትምህርት ቤት መሄድ አለባቸው፤ አሁን ባለው ሁኔታ ትምህርት ቤቶች ጥንቃቄ ያልተለያቸው ናቸው ብለዋል ፕሬዘዳንት አኩፎ አዶ፡፡
በምእራብ አፍሪካዊቷ ጋና በፈረንጆቹ የካቲት 16 ትምህርት ቤቶች የተዘጉት ሲሆን ሁለት ሰዎች በኮሮና መያዛቸውን ተከትሎ ነበር፡፡ በጋና እስካሁን 55ሺ በላይ ሰዎች የተያዙ ሲሆን 335 ሰዎች ሞተዋል፡፡