በአንድ የደቡብ አፍሪካ መሸታ ቤት 22 ሰዎች ሞተው ተገኙ
አደጋው የደረሰው በደቡብ አፍሪካ መዲና ኬፕታውን ከተማ ውስጥ ነው
ፖሊስ ጉዳዩን እየመረመረ ሲሆን የመዝናኛ ቤቱ የመደርመስ አደጋ አጋጥሞታል ተብሏል
በደቡብ አፍሪካ አንድ መሸታ ቤት 22 ሰዎች ሞተው ተገኙ፡፡
በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን በተለምዶ ለንደን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባለ አንድ ምሽት ቤት 22 ሰዎች መሞታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ በዚህ መሸታ ቤት እድሜያቸው ከ18 እስከ 20 ዓመት የሚሆናቸው ዜጎች በመሸታ ቤቱ ሞተው የተገኙ ሲሆን ጥቂት የማባሉ ደግሞ ከባድ እና ቀላል አደጋዎች አጋጥሟቸዋል፡፡
ወደ ሆስፒታል ከተወሰዱት ውስጥ ሁለቱ ለህይወታቸው በሚያሰጋ ሁኔታ ውስጥ ይገኙ የነበሩ ሁለት ወጣቶች መሞታቸውም ነው የተነገረው፡፡ ይህም ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የሟቾቹን ቁጥር 22 አድርሶታል፡፡
ብዙዎቹ ፈተና መጨረሳቸውን ተከትሎ ለተዝናኖት በሚል ወደ መሸታ ቤቱ ጎራ ያሉ ተማሪዎች እንደነበሩም የሃገሪቱ ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል፡፡ ሆኖም ወጣቶቹ ሞተው የተገኙበት ምክንያት አልታወቀም፡፡
የኬፕታውን ፖሊስ ኮሚሽነር ኖምቴቴለሊ ሊሊያን መሸታ ቤቱ ተደርምሶ በመዝናናት ላይ የነበሩት ወጣቶች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተናግረዋል፡፡ በአደጋው ምክንያት በተፈጠረ መረጋገጥ መሞታቸውም ነው የተነገረው፡፡
ሆኖም ተጎድተው መሞታቸው የሚያሳይ ምንም ዐይነት ነገር አለመኖሩ ሁኔታውን አወዛጋቢ አድርጎታል፡፡ መንስኤውን በውል ለማወቅ ምርመራ ላይ ነኝ ያለው የአካባቢው ፖሊስ የፎረንሲክ ናሙናዎችን ጭምር መውሰዱን ያስታወቀም ሲሆን የሟቾቹ አስከሬን በስፍራው ለተገኙ ቤተሰቦቻቸው አለመጠቱን ገልጿል፡፡
የአይን እማኞች የበርካታ ሰዎች አስከሬን በመዝናኛ ቤቱ ግቢ ውስጥ ማየታቸውን ተናግረው በህይወት ያሉ ተጎጂዎችን ወደ ህክምና በመወሰድ ላይ መሆናቸውን አክለዋል፡፡