ልዩልዩ
ደቡብ አፍሪካዊቷ የ128 ዓመት የእድሜ ባለጸጋ ረጅም እድሜ የመኖራቸውን ሚስጢር ተናግረዋል
አዛውንቷ ሁለቱንም የዓለም ጦርነቶችንና የእንግሊዝን የአፓርታይድ አገዛዝ ቁጭ ብለው አሳልፈዋል
የ12 ልጆች እናት የሆኑት አዛውንቷ 50 የልጅ ልጆች እንዳያቸው ተነግሯል
ጆና ማዜቡኮ በፈረንጆቹ ግንቦት 1894 በደቡብ አፍሪካ ኦስዳሌ ከተማ የተወለዱ ሲሆን አሁን ላይ 128 ዓመት ሆኗቸዋል።
ሁለቱንም የዓለም ጦርነቶችን እና የእንግሊዝን የአፓርታይድ አገዛዝ ቁጭ ብለው ያሳለፉት እኝህ አዛውንት በቀን ሁለት ጊዜ ብቻ እንደሚመገቡ ተናግረዋል።
ወተት እና ጎመን መሳይ አረንጓዴ ቅጠል (ስፒናች) አዘውትረው መመገባቸው ጤናማ እና ረጅም እድሜ ለመኖር እንዳገዛቸውም አዛውንቷ ተናግረዋል።
የ12 ልጆች እናት የሆኑት አዛውንቷ ከነዚህ ውስጥ ሶስቱ ብቻ በህይወት ያሉ ሲሆን 50 የልጅ ልጆች እንዳሏቸው የእንግሊዙ ሜትሮ ዘግቧል።
የልጅነት ምግባቸው እንደናፈቃቸው የሚናገሩት እኝህ አዛውንት ሁሉንም የህይወታቸውን ክስተቶች እንደሚያስታውሱት ተናግረዋል።
በህይወት ካሉ ረጅም የእድሜ ባለጸጋዎች መካከል ቀዳሚው ነኝ የሚሉት እኝሁ እናት ተፈጥሯዊ ምግቦችን ብቻ እንደሚመገቡም አክለዋል።
የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ እንደሚያስረዳው ፈረናሳዊቷ ጃኔ ልዊስ ካልመንት ረጅም ዓመት የኖሩ በሚል የተመዘገቡ ሲሆን 122 ዓመት ከ164 ቀናት በምድር ላይ በህይወት ቆይተዋል።