በደቡብ አፍሪካ “በጥቁር ተማሪ ደብተር ላይ የሸናው ነጭ ተማሪ” ከትምህርት ታገደ
ድርጊቱ ዘር ተኮር ግጭት ሊቀሰቅስ የሚችል አስነዋሪ ተግባር መሆኑ እየተነገረ ነው
ድርጊቱ ደቡብ አፍሪካ አሁንም ድረስ ዘረኝነትን ጨርሶ ያልጠፋባት ሀገር ለመሆኗ ማሳያ ነው ተብሏል
በደቡብ አፍሪካ ስተለንቦሽ ዩኒቨርሲቲ በጥቁር ተማሪ ደብተር ላይ የሸናው ነጭ ተማሪ ከትምህርት ቤት ታግዷል፡፡
ዩኒቨርሲቲው እርምጃው የወሰደው ነጭ ተማሪ በጥቁር ተማሪ ደብተር ላይ ሽንቱን ሲሽና የሚያሳይ ተንቀሳንቃሽ ምስል በማህበራዊ መዲያ ሲዘዋወር ካየ በኋላ ሲሆን፤ ድርጊቱ ዘር ተኮር ግጭት ሊቀሰቅስ የሚችል አስነዋሪ ተግባር ነው ሲል አውግዞታል፡፡
የዩኒቭረሲቲው ቃል አቀባይ ማርቲን ቪልጆን፡" ይህ አውዳሚ፣ጎጂ እና ዘር ተኮር ተግባር ነው" ሲሉ ድርጊቱን ኮንነውታል፡፡
ድርጊቱ የተፈጸመበት ጥቁር ተማሪ እስካሁን በድንጋጤ ውስጥ መሆኑነን የገለጹት ቃል አቀባዩ፤ የተፈጠረውን ነገር ለማጣራት ዩኒቨርሲተው የተለያዩ ጥረቶች እያደረገ መሆኑንም ተናግሯል፡፡
በተጨማሪ በጉዳዩ ላይ ምርምራ ላይ እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን፤ ነጩ ተማሪ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ ክስ ይመሰረትበታል ተብለዋል፡፡
ድርጊቱን ተከትሎ የዩኒቭረሲተው ተማሪዎች፤ በትናንትናው እለት ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ሲሆን ድርጊቱን ፈጽሞታል በተባለው የአንደኛ አመት ተማሪ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል፡፡
ድርጊቱ ሲፈጸም፤ ጥቁሩ ተማሪ በክፍሉ ተኝቶ እንደነበርና ሲነቃ በክፍሉ ማንም ሰው አለማየቱም የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ነው፡፡
በማህበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ ያለው ተንቀሳንቃሽ ምስል፤ ጥቁሩ ተማሪ ነጩ ተማሪን “ለምን ድብተሬ ላይ ትሸናለህ..?” ብሎ ሲጠይቀው የሚያሳይ ነው፡፡
ድርጊቱ ደቡብ አፍሪካ አሁንም ድረስ ዘረኝነትን ጨርሶ ያልጠፋባት ሀገር ለመሆኗ የሚያሳይ መሆኑን በርካቶች እየገለጹ ነው፡፡