በሱዳን ወታደራዊ አውሮፕላኖች ሲከሰከሱ በዚህ ዓመት ሁለተኛው ነው
በሱዳን አንድ ወታደራዊ አውሮፕላን ተከስክሶ የሰፖስት ሰዎች ህይወት አለፈ።
በዚህ አደጋ ከሞቱ ሰዎች መካከል አንድ የሌተናንት ኮለኔል ማዕረግ ያለው ወታደር እነደሚገኝበት ሲጂቲኤን አፍሪካ የሱዳንን ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት መግለጫን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
የጦር አውራፕላኑ የተከሰከሰው ከካርቱም በስተደቡብ በነጭ ናይል ግዛት አካባቢ ሲሆን በአውሮፕላኑ የተሳፈሩ ሁሉም ሰዎች ሀይወት እንዳለፈ ዘገባው ጠቁሟል።
በዚህ አደጋ ህይወታቸው ካጡ ዜጎች መካከክል የሶስት ሟቾች አስከሬን የተገኘ ሲሆን የሌሎች ሰዎች አስከሬን በመፈለግ ላይ መሆኑም ተጠቅሷል።
አደጋው ባሳለፍነው ረቡዕ ዕለት መድረሱ የተጠቆመ ሲሆን መን ያህል ዜጎች በአውሮፕላኑ ውስጥ እንደተሳፈሩ አስካሁን ይፋ አልተደረገም።
በሱዳን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወታደራዊ አውሮፕላኖች እየተከሰከሱ ወታደሮች እና ሲቪል ዜጎች እየሞቱ ነው።
ባሳለፍነው ጥር ተመሳሳይ አደጋ በዳርፉር ግዛት ተከስቶ የ16 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በተመሳሳይ ወር በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የጦር አውሮፕላን ተከስክሶ የጦር አውሮፕላኑ ሲከሰከስ ሶስት ወታደሮች ከአደጋው መትረፋቸውም ይታወሳል።
በፈረንጆቹ 2003 ዓመት የሱዳን ወታደራዊ አውሮፕላን ተከስክሶ የ116 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከኟቾች ወስጥ ስምንቱ የውጭ አገር ዜጎች ነበሩ።