ሚኒስትሩ በቫይረሱ መያዛቸውን ትናንት ቅዳሜ ነው ያስታወቁት
የሱዳን ጤና ሚኒስትር ዑመር አል ነጂብ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን አስታወቁ፡፡
ከሰሞኑ የበሽታው ምልክቶች ታተውባቸው እንደነበር ያስታወቁት ሚኒስትር በቫይረሱ መያዜ በምርመራ ተረጋግጧል ብለዋል፡፡
አል ነጂብ በቤት ውስጥ ውሸባ ገብተው ስራቸውን እየሰሩ ነው፡፡
“ቀደም ብዬ ለወሰድኳቸው ክትባቶች ምስጋና ይግባና እያገገምኩ እገኛለሁ”ም ብለዋል፡፡
ዜጎች ክትባቶቹን በመውሰድ የራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ጤና እንዲጠብቁም ነው ሚኒስትሩ ያሳሰቡት፡፡
37 ሺ 715 ሰዎች በቫይረሱ በተያዙባት ሱዳን የ2 ሺ 837 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡