ሱዳን የኢትዮጵያ አየመንገድን “ስም ለማጠልሸት” ተንቀሳቅሳለች፡ አምባሳደር ዲና
ምባሳደር ሲና ከሱዳን ጋር ድርድር ሊኖር የሚችለው ጦሯን ከኢትዮጵያ ሉአላዊ ግዛት ካስወጣች በኋላ ነው ብለዋል
ሱዳን በቅርቡ በኢትዮጵያ አየርመንገድ ተጭኖ ወደ ሀገሪቱ የገባ “የጦር መሳሪያ” ያዝኩ ማለቷ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቶ ነበር
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በቅርቡ የሱዳን መንግስት በኢትዮጵያ አየርመንገድ ተጭኖ ሱዳን የገባ “የጦር መሳሪያ” ያዝኩ ያለው የአየርመንገዱን “ስም ለማጠልሸት” ነው ብለዋል፡፡
የሱዳን መንግስት በቅርቡ በኢትዮጵያ አየርመንገድ ተጭኖ ወደ ሀገሪቱ የገባ የጦር መሳሪያ ያዝኩ ማለቱ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቶ ነበር፡፡
- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሱዳን የጫናቸው ጦር መሳሪያዎች “ህጋዊ የአደን ጦር መሳሪያዎች” መሆናቸውን አስታወቀ
- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ‘ጦር መሳሪያዎችንና ወታደሮችን ወደ ትግራይ አመላልሷል’መባሉን “መሰረተ ቢስ” ሲል አስተባበለ
- የኢትዮጵያ አየርመንገድ ወደ 19 ሀገራት የሚያደርገውን በረራ አቋረጠ
ነገርግን የሱዳን ጉምሩክ ባለስልጣናት ያዝን ያሉት “ጦር መሳሪያ” ራሳቸው በሰጡት ህጋዊ ፈቃድ ተጓጉዞ ወደ ካርቱም የገባ እንደሆነ የጦር መሳሪያዎቹ ባለቤት የሆነውና ‘ዋዒል ሸምሰዲን’ የተባለው የንግድ ተቋም መግለጹ ይታወሳል፡፡
የተቋሙ ጠበቃ የሆኑት ሲራጁዲን ሃሚድ ተያዙ የተባሉትን ጦር መሳሪያዎች በህጋዊ መንገድ የገቡ ናቸው ብለውም ነበር፡፡
ዋዒል ሸምሰዲን’ ለሲቪል ግልጋሎት የሚውሉ ጦር መሳሪያዎችን ከውጭ የማስገባት እና የመነገድ ፈቃድ ያለው ድርጅት ነው፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተገቢውን የህግ ሂደት ሳይጠብቁ ወደ ካርቱም ያስገባቸው ናቸው በሚል በማህበራዊ ሚዲያዎች ጭምር የሚናፈሰው መረጃ “ከእውነት የራቀ” መሆኑን መግለጹ ይታወሳል፡፡
አየር መንገዱ ወደ ሱዳን የጫናቸው ጦር መሳሪያዎች “ህጋዊ የአደን ጦር መሳሪያዎች” መሆናቸውንም ገልጿል፡፡
አምባሳደር ዲና ከወቅታዊ ጉዳይ በተጨማሪ በዘንድሮ አመት በዲፕሎማሲው ዘርፍ የነበሩ ስኬትና ፈተና ያሏቸውንም ጠቅሰዋል፡፡
አምባሳደሩ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሙሌት መከናውኑን በስኬት የገለፁ ሲሆን ግድቡ አለምአቀፋዊ የጸጥታ ጉዳይ ለማደረግ የነበረው ሙከራና በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ዙሪያ የነበረው የውጭ ጫና ፈተናዎች እንደነበሩ ገልጸዋል፡፡
በዘንድሮው አመት በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ግጭት እንደክፍተት በመቁጠር ሱዳን ወደ የኢትዮጵያ ድንበር ጥሳ መግባቷ የኢትዮጵያ መንግስት ሲገልጽ ቆይቷል፡፡ ምባሳደር ሲና ከሱዳን ጋር ድርድር ሊኖር የሚችለው ሀገሪቱ ጦሯን ከኢትዮጵያ ሉአላዊ ግዛት ካስወጣች በኋላ ነው ብለዋል፡፡