በጅቡቲ የባህር ጠረፍ በደረሰ የጀልባ መስጠም አደጋ ቢያንስ 38 ስደተኞች ሞቱ
በአብዛኛው ከአፍሪካ ቀንድ የመጡ 60 ሰዎችን የጫነችው ጀልባ ከተነሳች ከሁለት ሰአታት በኋላ ነበር የሰጠመችው
ኤጀንሲው ከአደጋው በህይወት የተረፉት 22 ሰዎች እርዳታ እየተገደረገላቸው ነው ብሏል
በጅቡቲ የባህር ጠረፍ በደረሰ የጀልባ መስጠም አደጋ ቢያንስ 38 ስደተኞች ሞቱ
በጅቡቲ የባህር ጠረፍ ባጋጠመ የጀልባ መስጠም አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 38 ሰዎች መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ(አይኦኤም) በዛሬው እለት አስታውቋል።
ኤጀንሲው እንደገለጸው በዚህ አደጋ ስድስት ሰዎች የደረሱበት ያልታወቀ ሲሆን በህይወት የተረፉት 22 ሰዎች እርዳታ እየተገደረገላቸው ነው።
የኤጀንሲው የቀጣናው ቃል አቀባይ ይቮኒ ንድጌ አደጋው ያጋጠመው ከጅቡቲ የባህር ጠረፍ 200 ሜትር ርቀት መሆኑን እና ጀልባዋ ሰኞ ጠዋት ከየመን መነሳቷን ተናግረዋል።
በአብዛኛው ከአፍሪካ ቀንድ የመጡ 60 ሰዎችን የጫነችው ጀልባ ከተነሳች ከሁለት ሰአታት በኋላ ነበር የሰጠመችው።
ቃል አቀባይዋ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ሳይሆኑ አይቀሩም ብለዋል።
"በየአመቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ በአብዛኛው ከኢትዮጵያ የሆኑ የአፍሪካ ቀንድ ስደተኞች ወደ ገልፍ ሀገራት ያቀናሉ" ሲሉ ንድጌ ተናግረዋል።ቨ
ቃል አቀባይዋ እንዳሉት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የመን ከደረሱ በኋላ ወደ ሌሎች የገልፍ ወይም የአረብ ሀገራት መሄድ ስለማይችሉ ጊዜ ለመግዛት በጅቡቲ ወደ ሀገሳቸው ይመለሳሉ።