በጫሞ ሀይቅ በደረሰው የጀልባ መስጠም አደጋ ህይወታቸውን ካጡ ሰዎች መካከል የሦስቱ አስከሬን ተገኘ
በጫሞ ሀይቅ በደረሰ የጀልባ መስጠም አደጋ የስምንት ሰዎች ህይወት አለፈ
ሰባት ጀልባዎችና ዋናተኞቸሰ የአስከሬን ፍለጋ እያደረጉ ነው ተብሏል
ቅዳሜ መጋቢት 16፤ 2015 ዓ.ም. በጫሞ ሀይቅ በደረሰ የጀልባ መስጠም አደጋ የስምንት ሰዎች ህይወት አልፏል።
በደቡብ ክልል ከአማሮ ልዩ ወረዳ ወደ አርባ ምንጭ ስምንት ሰዎችን አሳፍራ የነበረች ጀልባ መስጠሟን የወረዳው ኮሚኒኬሽን ገልጿል።
- በቱኒዚያ በደረስ የጀልባ መስጠም አደጋ የ23 ስደተኞች ህይወት አለፈ
- በቱርክ የርዕደ መሬት አደጋ በፍርስራሽ ተቀብራ የነበረች ሴት ከ3 ቀናት በኋላ በህይወት ተገኘች
የአደጋው መንስኤ የአየር ንብረቱ ጠንካራ መሆን እንደሆነ ለአል ዐይን የተናገሩት የአማሮ ልዩ ወረዳ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኃላፊ ሚልኪያስ ደቦጭ፤ "ማዕበልና ከፍተኛ ዝናብ" ጀልባዋ ለመስጠሟ ምክንያት መሆኑን አንስተዋል።
እየተደረገ ባለው የአስከሬን ፍለጋ እስካሁን የሦስት ወንዶች አስክሬን ተገኝቷል።
ሰባት ጀልባዎችን ጨምሮ በርካታ ዋናተኞች የቀሩትን የሦስት ወንድና የሁለት ሴቶች አስከሬን ፍለጋ እያደረጉ መሆኑንም ኃላፊው ገልጸዋል።
ሀይቁ ሰፊ መሆኑና የጣለው ከባድ ዝናብ ፍልጋውን ፈታኝ ማድረጉን ተናግረዋል።
ፍለጋው እስከመቼ እንደሚቀጥል እስካሁን አልታወቀም ያሉት ሚልኪያስ ደቦጭ፤ የፍለጋ ጀልባዎች ወደ ሰባት ከፍ መደረጋቸውን ገልጸዋል።
የአደጋው መንስኤን በተመለከተ ከአቅም በላይ ጭነት ነው የሚሉ ዘገባዎች የወጡ ቢሆንም፤ እስካሁን ይህን የሚያረጋግጥ መረጃ አለመገኘቱን ለአል ዐይን ተናግረዋል።