ዲሞክራቲክ ኮንጎ አለ የተባለውን የ”ወሲብ ጥቃት” ልትመረምር ነው
የዴሚክራቲክ ኮንጎ ዜግነት ላለቸው ሰራተኞች የሀገሪቱ መንግስት የተለየ ምርመራ ያደርጋል
የዓለም ጤና ድርጅትና አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት በራሳቸው ጉዳዩን ለመመርመር ቃል ገብተዋል
የዓለም ጤና ድርጅትና አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት በራሳቸው ጉዳዩን ለመመርመር ቃል ገብተዋል
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንደገለጸችው በጸረ-ኢቦላ ዘመቻ የተሰማሩ አለም አቀፍ ሰራተኞች በሀገሪቱ ሴቶች ላይ “ወሲባዊ ጥቃት” አድርሰዋል የሚለውን ክስ ላይ ምርመራ እጀምራለሁ ብላለች፡፡
ባለፈው አመት የቀረበው ሪፖርት እንደሚያመለክተው ከ10 በርካታ ቁጥር ሴቶች ከተባbሩት መንግስታት ድርጅት በመጡ የጤና ድርጅት የእርዳታ ሰራተኞች ጥቃት እንደደረሰባቸው ገልጸዋል፡፡
እንደ ሪፖርቱ ከሆነ በፈረንጆቹ 2018-2020 በተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ወቅት ነው “ወሲባዊ ጥቃት” አድርሰዋል የሚል ክስ ነው የቀረበው፡፡
“የኮንጎ መንግስት እርምጃ ይወስዳል፤ ወደ ሰሜን የሀገሪቷ ክፍል የሚሄድ የምርመራ የሚላክ ቡድን አቋቁመናል“ ብለዋል የጤና ሚኒስትር የሆኑት ኢተኒ ሎንጎንዶ፡፡
በምርመራው ጥፋት ያጠፋው ይቀጣል ብለዋል ሚንስትሯ፡፡
የዓለም ጤና ድርጅትና አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት በራሳቸው ምርመራ ለመጀመር ቃል ገብተዋል፡፡
ሚኒስትሯ እንዳሉት የዴሚክራቲክ ኮንጎ ዜግነት ላለቸው ሰራተኞች የሀገሪቱ መንግስት የተለየ ምርመራ በማድረግ እንደዚህ ባህሪን ለመከላል ይሰራል ብለዋል፡፡