ልዩልዩ
በማጉፉሊ የአስከሬን ሽኝት ስነ ስርዓት ላይ በተፈጠረ መረጋገጥ የ45 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ
ሳሚያ ስሉሁ ሃሰን 6ኛዋ የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መሃላ መፈጸማቸው ይታወሳል
በመረጋገጡ ተጨማሪ 37 ሰዎች ለጉዳት መዳረጋቸውም ተነግሯል
በቅርቡ ከዚህዓለም በሞት በተለዩት የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ጆን ፖምቤ ማጉፉሊ የአስከሬን ሽኝት ስነ ስርዓት ላይ በተፈጠረ መረጋገጥ የ45 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ፡፡
መረጋገጡ ባሳለፍነው እሁድ መጋቢት 12 ቀን 2013 ዓ/ም በሃገሪቱ ዋና ከተማ ዳሬ ሰላም በሚገኘው የኡሁሩ ስቴዲዬም በነበረው የመጨረሻ የአስከሬን ሽኝት ስነ ስርዓት ላይ ያጋጠመ ነው፡፡
ወደ ስቴዲዬሙ በመግባት የሽኝት ስነ ስርዓቱን ለመታደም ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ተጨማሪ 37 ሰዎች መጎዳታቸውም ይፋ ሆኗል፡፡
በርካቶች ከመግቢያ በሮች ውጭ በአጥር ጭምር በመንጠላጠል ወደ ስቴዲየሙ ለመግባት ሲጋፉ ነበር ነው የተባለው፡፡
ይህም ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ህጻናት ጭምር እንዲረጋገጡ በአየር እጦት ለመተንፈስ እንዲቸገሩ አድርጓል፡፡
የ61 ዓመቱ ማጉፉሊ “በልብ ህመም ምክንያት” ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው እና ስርዓተ ቀብራቸው በትውልድ ቀያቸው መፈጸሙ የሚታወስ ነው፡፡
ሳሚያ ስሉሁ ሃሰን 6ኛዋ የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መሃላ መፈጸማቸውም አይዘነጋም፡፡