የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት በእስር ላይ ለነበሩ 1700 ኢትዮጵያውን ይቅርታ አደረጉ
በባለፈው አመትም ከአውሮፓ ህብረት ጋር በተባበር በርካታ ኢትዮጵያውን ተመልሰው ነበር
ፕሬዝዳንቱ ይቅርት ያደረጉት ወደ ታንዛኒያ ካቀኑት ፕሬዝዳንት ሳህለ-ወርቅ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ነው ተብሏል
የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ማጉፉሊ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገሪቱ በመግባታቸው ምክንያት ታስረው የሚገኙ 1,789 ኢትዮጵያውያን እንዲለቀቁ አዘዙ፡፡
ፕሬዘዳንቱ ይህን ወሳኔ ያስተላለፉት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ታንዛኒያ ካቀኑት የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ሳህለ-ወርቅ ዘውዴ ጋር ከተወያዩ በኋላ መሆኑን ኔሽን ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
“ኢትዮጵያውያን ከፈለጉ ዛሬ ወደ ቤታቸው መሄድ ይችላሉ” ያሉት ፕሬዝዳንቱ ትክክለኛ የጉዞ ሰነድ ያጡ የውጭ ዜጎች እንዲያጡ አይገደዱም ብለዋል፡፡
ኢትዮጵዮጵያውኑ ወደ ታንዛኒያን እንደ መሸጋገሪያ በማድረግ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናት አስበው ነበር ተብሏል፡
ባለፈው ዓመት በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የአውሮፓ ህብረት-አይኦኤምና በአፍሪካ ቀንድ የስደተኞች ጥበቃ እና መልሶ ማቋቋም ኢዩ-አይኦኤም በተደረገው ድጋፍ ከታንዛኒያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል ፡፡
በአውሮፓ ህብረት የአስቸኳይ ጊዜ ትረስት ፈንድ ለአፍሪካ የተደገፈው ተነሳሽነት ከ 26 የአፍሪካ አገራት ጋር በጠበቀ ትብብር ተቋቁሟል ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዳስታወቀው ህገ-ወጥ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው ያመጣቸው መርሃ ግብር የአውሮፓ ህብረት እና አይኦኤም የጋራ ትብብር ሲሆን ይህም በስደተኞች አሰላለፍ ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ፣ መደበኛ እና ኃላፊነት የሚሰማውን አያያዝ ያመቻቻል ፡፡
ይህ በመብቶች ላይ የተመሠረተ እና በልማት ላይ ያተኮሩ ፖሊሲዎችን እና ጥበቃን እና ዘላቂ መልሶ ማቋቋም ላይ በማጎልበት ይሰራል፡፡