በናይጀሪያ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ላይ በተከፈተ ጥቃት ቢያንስ 50 ሰዎች ተገደሉ
የአጥቂዎቹ ማንነት እና ዓላማ እስካሁን አልተገለጸም
የናይጀሪያው ፕሬዝደንትሙሃማዱ ቡሃሪ ጥቃቱን “አስከፊ” ሲሉ አውግዘዋል
በደቡብ ምዕራብ ናይጄሪያ ውስጥ ታጣቂዎች እሁድ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ላይ በከፈቱት የጅምላ ጥቃት ሴቶች እና ሕፃናትን ጨምሮ ቢያንስ 50 ሰዎችን መግደላቸውን የሆስፒታል ምንጮች እና ዶክተሮች ተናግረዋል፡፡
ታጣቂዎቹ በቤተክርስቲያኑ ህንጻ ውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ በጥይት በመተኮስ ምእመናንን ገድለዋል፣ አቁስለዋል ሲል ል ሲል የኦንዶ ግዛት ፖሊስ ቃል አቀባይ ፉንሚላዮ ኢቡኩን ኦዱንላሚን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የፖሊስ ኃላፊዋ በኦቮ ከተማ በሚገኘው የቅዱስ ፍራንሲስ ካቶሊካዊ ቤተክርስቲያን ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉ እና እንደተጎዱ ባይገልጹም፤ ፖሊስ የጥቃቱን መንስኤ እያጣራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ጥቃቱ የተፈጸመበትን ቦታ የጎበኑት የኦንዶ ግዛት አስተዳዳሪ አራኩሪን ኦላዋሮቲሚ አኬሬዶሉ ጥቃቱ የእሁድ ክስተት "ትልቅ እልቂት" እንደሆነ ገለጸው ይህ ክስተት ድጋሚ እንዲከሰት መፈቀድ የለበትም ብለዋል፡፡
የአጥቂዎቹ ማንነት እና ዓላማ እስካሁን አልተገለጸም።
በናይጄሪያ የሚገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ቃል አቀባይ ሬቨረንድ አውጉስቲን ኢክኩ “የቅዱስ ቅዳሴ ሥነ ሥርዓቱ በሚካሄድበት ወቅት ያልታወቁ ታጣቂዎች በቅዱስ ፍራንሲስ ካቶሊካዊ ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት ማድረጋቸው በጣም አሳዛኝ ነው…”::
ኢኩዌ እንደተናገሩት ጳጳሱ እና የደብሩ ካህናት ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ከጥቃቱ ተርፈዋል።
በኦቮ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ዶክተር ለሮይተርስ እንደተናገሩት በጥቃቱ ቢያንስ 50 የሚሆኑ አስከሬኖች በከተማዋ በሚገኙ ሁለት ሆስፒታሎች ገብተዋል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ዶክተሩ፣ የተጎዱትን ለማከም የደም ልገሳ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡