በመጭው ግንቦት 12 ሀገራዊ ምርጫ የምታካሂደው ቡሩንዲ የአለም ጤና ድርጅት ሰራተኞች ሀገሪቱን ለቀው እንዲውጡ አዘዘች
በመጭው ግንቦት 12 ሀገራዊ ምርጫ የምታካሂደው ቡሩንዲ የአለም ጤና ድርጅት ሰራተኞች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች
ቡሩንዲ በሀገሪቱ የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ የሆኑትን እና ሌሎቸ ሶስት የድርጅቱ ሠራተኞች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ መወሰኗ ተገለጸ፡፡
የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ረዳት በርናንድ ንታሂራጃ የድርጅቱ ስራተኞች ከቡሩንዲ ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ መተላለፉን ገልጸው ምክንያቱን ግን ይፋ አለማድረጋቸው ተሰምቷል፡፡
በሚቀጥለው ሳምንት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደምታደርግ የገለጸችው ቡሩንዲ የኮሮና ቫይረስ በተስፋፋበትና ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ሆኖ ሳለ የዓለም ጤና ድርጅት ባለድረቦችን ከሀገሯ እንዲወጡ ማዘዟ አነጋጋሪ ሆኗል ነው የተባለው፡፡
የቡሩንድ መንግስት ከሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ረቡዕ ዕለት የተጻፈው ደብዳቤ በሀገሪቱ ለዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ካዛዲ ሙሎምቦ ደርሷ ተብሏል፡፡በዚህም መሰረት የድርጅቱ ሰራተኞች ነገ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል፡፡
ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የታዘዙት የወረርሽኝ አጥኚው ጂያን ፔይሬ ሙሉንዳ ንካታ፣የጤና ዘርፍ አስተባባሪ ሩሃና ሚሪንዲ ቢሲምዋ እና ዳንኤል ታርዚ ናቸው፡፡ በፈረንጆቹ የፊታችን ግንቦት 20 ምርጫ የምታደርገው ቡሩንዲ ለምርጫ የሚወዳደሩ ዕጩዎች ቅስቀሳ እያደረጉ ናቸው፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ማትሽዲሾ ሞአቲ በቡሩንዲ ያሉት ባልደረባቸው ጎበዝና ችሎታ ያላቸው ናቸው ሲሉ በአዲስ አበባ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ምስክርነት መስጠታቸው ይታወሳል፡፡
ቡሩንዲ እስካሁን 27 ሰዎች በኮሮና ሲያዙባት አንድ ሰውም ለህልፈት ተዳርጓል ተብሏል፡፡ ይሁንና 11 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ቡሩንዲ እስካሁን የመረመረችው 527 ሰዎችን ብቻ መሆኑን የአፍሪካ በሽጻ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል አስታውቋል፡፡
የማዕከሉ ኃላፊ ዶ/ር ጆን ነኬነጋሶንግ አሁን ላይ የኮሮና ወረርሽኝ ሥጋት በሆነበት ሁኔታ ቡሩንዲ ምርጫ ለማድረግ ማሰቧ አሳዛኝ መሆኑን አንስተዋል፡፡“ አሁን ላይ ተባብረን ይህንን ወረርሽኝ መከላከል አለብን”ሲሉም የቡሩንዲን ውሳኔ ተችተዋል፡፡
በቡሩንዲ ሊካሄድ የታሰበው ምርጫ ኮሮናን እንዳያባብስ ተሰግቷል፡፡ቡሩንዲ በ2018 በሀገሪቱ ያለውን የመብት ጥሰት ለመመርመር ወደ ሀገሯ መጥተው የነበሩትን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባልደረቦች ማባረሯ ይታወሳል፡፡