በምዕራብ አውሮፓ ሀገራት በደረሰ የጎርፍ አደጋ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ90 አለፈ
በጎፍር አደጋው ጀርመን ብቻ ከ80 በላይ ሰዎች ህይወት ማፉ ተነግሯል
የጎርፍ አደጋው በርካታ ሰዎች መጥፋታቸውም ነው እየተነገረ ያለው
በምዕራብ አውሮፓ ሀገራት በደረሰ የጎርፍ አደጋ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ90 ማለፉ ተገለፀ።
በጀርመን በደረሰው የጎርፍ አደጋው ከ80 በላይ ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን፤ በርካቶች እስካሁን የገቡበት እንዳልታወቀ እና የማፈላግ ስራ እተካሄደ መሆኑም ታውቋል።
የጎርፍ አደጋው በተለይም በረሂንላንድ ፐላቲናቴ እና በሰሜን ርሂን ዌስትፋሊያ ከባድ ጉዳት ማድረሱ የተገለጸ ሲሆን፤ በርካታ ህንፃዎች እና ቆመው የነበሩ ተሸከርካሪዎች በጎርፍ መወሰዳቸውም ታውቋል።
ከአሜሪካው ፐሬዚዳንት ጋር ለመምከር ኒውዮርክ የሚገኙት የጀርመኗ መራሄተ መንግትስ አግላ ሜርክል በበኩላቸው፤ “አደጋው አስደንጋጭ እና አሳዛኝ ነው” ማለታቸው ተሰምቷል።
በጎርፍ አደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው የሀገሪቱ ዜጎችም አስፈላጊ የሆኑ ድጋች በሙሉ እንደሚደረግላቸውም ነው የጀርመኗ መራሄተ መንግትስ ያስታወቁት።
በተመሳሳይ በቤልጂየምም በጎርፍ አደጋው የ11 ሰዎች ሕይወት ላመፉንም ነው የሮይተርስ ዘገባ የሚያመለክተው።
በኔዘርላንድም የጎርፍ አደጋው ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ የተገለጸ ሲሆን፤ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ባይደርስም በርካታ ህንፃዎች እና ተሸከርካሪዎች በጎርፍ መወሰዳቸው ተነግሯል።
በጎርፍ አደጋው ህይወታቸውን ካጡ ሰዎች በተጨማሪ በርካቶች መጥፋታቸው እና በጎርፍ ተከበው በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ የቤታቸው ጣራ ላይ ተቀምጠው እርዳታ የሚጠባቁ እንዳሉም ተነግሯል።
የጎርፍ አደጋው በምዕራባዊ የአውሮፓ ሀገራት የጣለውን ክብረወሰን የሆነ ከባድ ዝናብ ተከትሎ ወንዞች ሞልተው በመፍሰሳቸው ነው የደረሰው።
ፖለቲከኞች የጎርፍ አደጋው ዋነኛ መንስኤ የአየር ንረት ለውጥ ነው ያሉ ሲሆን፤ ተመራማሪዎች በበኩላቸው አየር ንብረት እተለወጠ በሄደ ቁጥር ተፈጥሮ አደጋዎች እያጋጠሙ ይሄዳሉ፤ ነገር ግን አንድን አደጋ ለብቻው ከከባ አየር ለውጥ ጋር ማያያዝ አስቸጋሪ ነው ብለዋል።