ከ7200 ሄክታር በላይ ሰብል ጠፍቷል፤ ከ691ሺ በላይ ከብቶችና ዶሮዎች ሞተዋል ወይም በጎርፍ ተወስደዋል
ከ7200 ሄክታር በላይ ሰብል ጠፍቷል፤ ከ691ሺ በላይ ከብቶችና ዶሮዎች ሞተዋል ወይም በጎርፍ ተወስደዋል
በቬትናም ከአስርት አመታት ወዲህ በተከሰተ ከባድ ጎርፍ 100 ሰዎች የሞቱ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ሰጥመዋል፤ ባለስልጣናት የአየር ሁኔታው ሊከብድ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡
ለሳምንታት በቆየው ጎፍና የመሬት መንሸራተት 111 ሰዎች መሞታቸውንና 22 ሰዎች መጥፋታቸውን ሲኤንኤን ሮይተርስን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡ የቬትናም የቀይ መስቀል ፕሬዘዳንት የሆኑት ንጉየን ቲዡን ዡ ከበርካታ አስርት አመታት ከታየው የከፍ ጎርፍ መከሰቱን ተናግረዋል፡፡
ከ7200 ሄክታር በላይ ሰብል ጠፍተዋል፤ ከ691ሺ በላይ ከብቶችና ዶሮዎች ሞተዋል ወይንም በጎርፍ መወሰዳቸውን የቬትናምን ዜና አገልግሎት ጠቅሶ ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡ 16 ብሄራዊ መንገዶችና 161ሺ የአካባቢ መንገዶች በአራት ግዛቶች ከጥቅም ውጭ ሆነዋል፡፡
ሀገሪቱ አሁን ፊሊፕንስን አጥቅቶ ለመጣው የትሮፒካል ስቶርም እየተዘጋጀች ነው፡፡ በፊሊፕንስ ከፍተኛ ጎርፍ ተከስቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲሰደዱ ሆኗል፡፡
የጥቅምት ወር በቬትናም የዝናብ ወቅት ተብሎ የሚወሰድ ቢሆንም ለሳምንታት የግብርና፤የትራንስርትና የመስኖ አገልግሎትን የጎዳ ደረቅ ወቅት ነበር፡፡ በወሩ መጀመሪያ የተከሰተው ንፋስ ዝናብና ጎርፍን ሊያስከት ችሏል፡፡
በስድስት ግዛቶች የሚገኙ ከ250ሺ በላይ ነዋሪዎች ተጥለቅልቀዋል፤ከጥቅምት አጋማሽ ጀምሮ 2ና 3 ሶስት ሜትር ውሃ ውስጥ ገብተው ቆይተዋል፡፡