አደጋው የደረሰበት ፋብሪካ በሕገወጥ መንገድ የተቋቋመ ነው ተብሏል
በሞሮኮ ታንጂየር ከተማ በሚገኝ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ በከባድ ዝናብ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ28 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ የሟቾቹ እድሜ ከ20 እስከ 40 እንደሆነ ተዘግቧል፡፡
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከፋብሪካው ምድር ቤት ከሚገኝ አንድ የመኖሪያ ቪላ ውስጥ 10 ሰዎችን አድነዋል፡፡ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞቹ በድንገት በተከሰተው ጎርፍ የተጠለፉ ተጨማሪ ሰዎች ካሉ በሚል የማፈላለግ ስራ በመስራት ላይ ናቸው፡፡
ፋብሪካው በሕገ ወጥ መንገድ የተከፈተ ሲሆን በቦታው የሚገኙ አጠቃላይ የጉልበት ሠራተኞች ቁጥር በትክክል እንደማይታወቅ እና ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ዘ ናሺናል ዘግቧል፡፡
ከቻይና እና እና የቱርክ ምርቶች ጋር ለመወዳደር ፣ በሞሮኮ በተለይም በካዛብላንካ እና ታንጂየር ከተሞች በርካታ ፋብሪካዎች ከመንግስት እይታ ተሰውረው በመኖሪያ መንደሮች አካባቢ ስራቸውን እንደሚያከናውኑ ተገልጿል፡፡
እያንዳንዱ ህገወጥ ፋብሪካ እድሜያቸው ያልደረሰ ህጻናትን ጨምሮ እስከ 40 ሰራተኞችን እንደሚቀጥር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡