ዩክሬንም ከሁለት ሳምንት በፊት ከሶሪያ ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጧ ይታወሳል
ሶሪያ ይህንን እርምጃ የወሰደችው ከሳምንታት በፊት ዩክሬን ተመሳሳይ ድርጊት መፈጸሟን ተከትሎ መሆኑንም ተገልጿል፡፡
ሶሪያ በምስራቃዊ ዩክሬን ዶንባስ ለሚገኙት የሉሃንስክ እና የዶኔስክ ተገንጣዎች ሀገራቸው ከዳማስቆ ጋር ያላት ግንኙነት መቋረጡን ገልጠው እንደነበር ይታወሳል፡፡
ዩክሬን፤ ለተገንጣዮች እውቅና ሰጥታለች ካለቻት ሶሪያ ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን መግለጿ የሚታወስ ሲሆን ሶሪያም አጸፋውን መልሳለች፡፡
የሶሪያው ፕሬዝዳንት ባሽር አልአሳድ ከሩሲያ ጋር ያላቸው ግንኙነት የጠበቀ ሲሆን በጦርነቱም የሞስኮ ደጋፊ ናቸው፡፡ ሞስኮም ብትሆን ባሽር አልአሳድ አሜሪካና አጋሮቿ ከምትደግፋቸው አማጺያን ጋር ሲዋጉ ድጋፍ ሲያደርጉላቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡
ሶሪያ በፈረንጆቹ ሰኔ 29 ቀን 2022 ለሉሃንስክ እና ዶኔስክ ግዛቶች ዕውቅና መስጠቷ ይታወሳል፡፡