የእስራኤል አየር ኃይል በደማሰቆ ከተማ እና በጎላን ተራራዎች ላይ ጥቃት ፈጽሟል
እስራኤል አየር ኃይል በደማስቆ እና በጎላን ተራሮች ላይ የአየር ድብደባ መፈጸሙን ሶሪያ ገለፀች።
የሲሪያ መንግስት የመገናኛ ብዙሃን ይዘው በወጡት መግለጫ፤ የእስራኤል አየር ጥቃት ዛሬ ማለዳ ላይ መፈጸሙን አስታውቀዋል።
በሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆ ላይ የተቃጠውን የአየር ድብደባ የሶሪያ የአየር መከላከያ ምለሽ እየሰጠው መሆኑንም ገልጸዋል።
የሶሪያ የዝና አገልግሎትሱና በበኩሉ፤ የእስራኤል አየር ኃይል ዛሬ ማለዳ ላይ በአወዛጋበዊው የጎላን ተራራ እና በተወሰኑ የደማስቆ ከተማ ስፍራዎች ላይ የአየር ጥቃት መፈፀሙን አስታውቋል።
የእስራኤል አየር ኃይል ከአየር ላይ ሚሳዔሎችን ያስወነጨፈ ሲሆን፤ አብዛኞችም በአየር መከላከያ ስርዓት እንዲከሽፉ መደረጉንም ሱና ዘግቧል።
እስራኤል የፈፀመችውን የአየር ጥቃት ተከትሎም ሶስት የሶሪያ ወታፈሮች መገደላቸውን እና ሰባት ደግሞ መቁሰላቸውን የዘገበው ሱና፤ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱንም አስታውቋል።
ስለ አየር ድብደባው በእስራኤል በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።
እስራኤል ባለፉት ዓመታት በሶሪያ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአየር ጥቃቶችን እንደፈፀመች የሚነገር ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ እውቅና የሰጠችው ለጥቂቶቹ ብቻ ነው።
በፈረንጆቹ 2020 ብቻ በሶሪያ ላይ ከ39 በላይ የአየር ድብደባዎችን ፈጽማለች የተባለ ሲሆን፤ እስራኤል የአየር ድብደባው ኢላማዎች በሶሪያ ድንብር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የኢራን ሚሊሻዎችን ኢላማ ያደረገ ነው ትላች።