ፕሬዝዳንት ጆ ቫይደን ግለሰቡ በሶሪያ ኢድሊብ በተባለችው ገዛት በተደረገ ዘመቻ መገደሉን አስታውቀዋል
የአሜሪካ ጦር የአይኤስ መሪ የሆነውን አቡ ኢብራሂም አል ሃሺሚ አልቁራይሽን መግደሉን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አስታወቁ፡፡
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ባይደን የአይኤስ መሪ እንደነበረ የገለጹት ግለሰብ በሶሪያ ኢድሊብ በተባለችው ገዛት በተደረገ ዘመቻ መገደሉን ገልጸዋል፡፡
አቡ ኢብራሂም አልሃሺሚ አል ቁራይሺ አሜሪካ ባካሄደችውን ወታደራዊ ተልዕኮ መከናወኑ የተገለጸ ሲሆን ለዘመቻው የተላኩትም በሰላም መመለሳቸውን ዋሸንግተን ገልጻለች፡፡
ጆ ባይደን፤ የሀገራቸው ወታደሮች “ብቃትና ብልሃት” የሚደነቅ እንደሆነ ገልጸው በተልዕኮው ላይ የተሳተፉት አሜሪካውያን በሰላም መመለሳቸውንም ገልጸዋል፡፡ በኢድሊብ በተደረገው ወታደራዊ ተልዕኮ አሜሪካ አሸባሪ ካለቻቸው የአይ ኤስ አባላት ባለፈም 13 ሕጻናትና ሴቶች መገደላቸው ተዘግቧል፡፡
ወታደራዊ ተልዕኮው ያተኮረው የ”አሸባሪው ቡድን መሪ” እና ከእርሱ ጋር የተባበሩትን መሆኑን የገለጸችው አሜሪካ ተልዕኮው የተካሄደው በተዋጊ ጀት እና በሄሊኮፍተር እንደነበረም ገልጻለች፡፡
አሜሪካ ይህ ወታደራዊ ተልዕኮ የተደረገው፤ አሜሪካን እና አጋሮችን ለመጠበቅ መሆኑን አስታውቃለች፡፡
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታጎን) ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ የደረገው ወታደራዊ ተልዕኮ የተሳካ እንደነበር ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ ቃል አቀባዩ ከአሜሪካ በኩል ምንም አይነት ጉዳት እንዳላጋጠመ ገልጸው ተጨማሪ መረጃ እንደተገኘ እንደሚገለጽ ተናግረዋል፡፡
ፕንታጎን በወታደራዊ ተልዕኮው ንጹሃን መገደላቸውን በተመለከተ የገለጸው ነገር የለም ተብሏል፡፡