ዩኤኢ በሶሪያ ፀጥታ መረጋጋትና አንድነት እንዲመጣ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ገለጸች
የዩኤኢ ውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዳማስቆ ገብተዋል
የተባሩት አረብ ኢሚሬቶች በሶሪያ ፀጥታ፣ መረጋጋትና አንድነት እንዲመጣ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት አስታወቀች
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ( ዩኤኢ) የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ሼክ አብዱላህ ቢንዛይድ አል ናህያን ዳማስቆ ከተማ መግባታቸው ተገልጿል፡፡
ሚኒስትሩ ከሶሪያ ፕሬዝዳንት ባሽር አል አሳድ ጋር ተገናኝተው መወያየጣቸውን የተባበሩት አረን ኢሚሬቶች ዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡ አቡዳቢ፤ በሶሪያ ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም አንድነት እንዲመጣ ጽኑ ፍላጎት እንዳላት ሚኒስትሩ መናገራቸው ተዘግቧል፡፡
ሼክ አብዱላህ ቢንዛይድ አል ናህያን ከሶሪያው ፕሬዝዳንት ባሽር አል አሳድ ጋር በዳማስቆ ባደረጉት ውይይት የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት ለማጠናከር ተወያይተዋል ተብሏል፡፡
ዩኤኢ፤ በሶሪያ ግጭት እንዲቆምና ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ለሚያደርጉ ሁሉም ጥረቶች ድጋፍ እንደምታደርግም ሼክ አብዱላሂ ገልጸዋል፡፡ እነዚህ ጥረቶችም የሶሪያውያን የልማት፣ የዕድገትና የልማት ፍላጎቶች እንዲሳኩ እንደሚያደርግ ተዘግቧል፡፡
የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብት ሚኒስትሩ የዩኤኢ መሪዎች በሶሪያ መረጋጋት፣መሻሻል እና ብልጽግና እንዲመጣ መመኘታቸውን ለሶሪያው ፕሬዝዳንት ገልጸውላቸዋል ተብሏል፡፡
የሶሪያው ፕሬዝዳንት ባሽር አል አሳድ በበኩላቸው ዩኤኢ ለሁለቱ ሀገራት ሕዝብ ወዳጅነት መጠናከር ያደረገችውን አስተዋጽኦ አድንቀዋል ተብሏል፡፡ የውጭ ጉዳይና ትብብር ሚኒስትሩ ጉብኝት የሀገራቱን ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር እንደሚያደርገው ተገልጿል፡፡ ዩኤኢ እና ሶሪያ በተለያዩ ዘርፎች ላይ በጋራ ትብብሮች ላይ ላይ እንደሚሰሩ መግለጻቸውም ተዘግቧል፡፡
ሁለቱ ወገኖች በመካከለኛው ምስራቅ እና በሶሪያ እንዲሁም በቀጣናዊ እና በዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ባሉ አዳዲስ ጉዳዮች ላይም ተነጋግረዋል ተብሏል፡፡ የዩኤኢ ከፍተኛ ባለስጣን ከ10 ዓመት በበለጠ ጊዜ ሶሪያን ሲጎበኝ ሼክ አብዱላህ ቢንዛይድ አል ናህያን የመጀመሪያ ናቸው ተብሏል፡፡