አትሌት ለተሰንበት በፈረንጆቹ 2019 በኳታር ዶሃ በተካሄደው የ10ሺ ሜትር ውድድር የብር ሜዳሊያ አሸንፋ ነበር
አትሌት ለተሰንበት በፈረንጆቹ 2019 በኳታር ዶሃ በተካሄደው የ10ሺ ሜትር ውድድር የብር ሜዳሊያ አሸንፋ ነበር
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ በሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ለ12 አመታት ተይዞ የነበረውን የ5ሺ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን በትናንትናው ምሽት በስፔን በተካሄደ ውድድር ስብራለች፡፡
አትሌት ለተሰንበት የ5ሺ ሜትር ለማጠናቀቀ 14:06:62 የፈጀባት ሲሆን ጥሩነሽ ዲባባ በቤጂንግ 14:11:15 ነበር ያጠናቀቀችው፡፡
አትሌት ለተሰንበት በፈረንጆቹ በ2015ና በ2017 ከ20 አመት በታች የአለም አቀፍ ውድድር ማሸነፍ ችላ ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለተሰንበት በፈረንጆቹ 2019 በኳታር ዶሃ በተካሄደው የ10ሺ ሜትር ውድድር የብር ሜዳሊያ ማግኘቷ ይታወቃል፡፡
በስፔን በተካሄደው ውድድር አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ለ15 ዓመታት ይዞት የነበረው የ10 ሺ ሜትር ክብረወሰንም ክብረወሰኑ በኡጋንዳዊው አትሌት ጆሽዋ ቼፕቴጌ ተሰብሯል፡፡
በስፔን እየተካሄዱ ያሉት ውድድሮች እንደቀጠሉ ናቸው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የአለም ክብረወሰን ላስመዘገበችው ለተሰንበት ”አኩርተሽናል፣ እንኳን ደስ ያለሽ” የሚል መልእክት በፌስ ቡክ ገጻቸው ጽፈዋል፡፡