የሱዳን መንግስትና አማጺያኑ ያለመዘግየት ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ቃል ገቡ
ደቡብ ሱዳን መንግስትን ከዳርፉር፣ከሳውዝ ኮርዶፋንና ከብሉ ናይል አማጺያኖች ጋር ለማደራደር ስትሰራ ቆይታለች
ስምምነቱ በሱዳን ዳርፉር የነበረውን የ17ዓመት ጦርነትና በሳውዝ ኮርዶፋንና ብሉ ናይል የነበረውን ለ9 አመት የቆየውን ጦርነት እልባት ሰጥቷል
ስምምነቱ በሱዳን ዳርፉር የነበረውን የ17ዓመት ጦርነትና በሳውዝ ኮርዶፋንና ብሉ ናይል የነበረውን ለ9 አመት የቆየውን ጦርነት እልባት ሰጥቷል
የሱዳን መንግስትና አማጺያን በስምምነቱ መጨረሻ ያሰፈሯቸውን ነጥቦች ያለመዘግየት ወደ ተግባር ለመቀየር በትናንትናው እለት ቃል ቀገብተዋል፡፡
መንግስትና አማጺያኑ የመጨረሻ የተባለውን ስምምነት ከፈረሙ በኋላ በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ቃል መግባታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
መንግስትን በመወከል ሲደራደሩ የነበሩት ሞሀመድ አል ሃሰን አል ቲያሺ “ሁለቱ ወገን በፈራሚዎች መካከል አንድነት አንዲኖር ተስማምተናል፡፡ በስምምነቱ የተካተቱትን የትኞቹንም ነጥቦች ያለምንም መዘግየት ተግባራዊ ለማድረግ ተስማምተናል” ብለዋል፡
ሞሀመድ እንደተናገሩት የሱዳን ህዝብ ጦርነቱ አልቋል የሚለውን ለማረጋገጥ የስምምነቱን ተግባራዊነት የጸጥታ ስራ መስራት አንደሚጀመሩ ገልጸዋል፡፡ የዘጠኝ አማጺ ኃይሎች ጥምረት የሆነው የሱዳን ሪቮሉሽናሪ ግንባር መሪ የሆኑት አልሃሚድ እድሪስ ለስምምነቱ ተግባራዊነት ያላቸውን ጹኑ እምነት ገልጸዋል፡፡
መንግስትና አማጺያኑ የመጨረሻ የተባለውን የሰላም ስምምነት የተፈራረሙት ባለፈው ቅዳሜ በቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ነበር፡፡ ስምምነቱ በሱዳን ዳርፉር የነበረውን የ17ዓመት ጦርነትና በደቡብ ኮርዶፋንና ብሉ ናይል የነበረውን ለ9 አመታት የቆየውን ጦርነት እልባት ሰጥቷል፡፡
እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ በፈረንጆቹ 2003 የፈነዳው የዳርፍር ጦርነት 300ሺ ሰዎች እንዲሞቱና 2.5 ሚሊዮን ሰዎች አንዲሰደዱ ምክንያት ሆኗል፡፡ በደቡብ ኮርዶፋንና በብሉ ናይል በተካሄደው ጦርነት አንድ ሚሊዮን ሰዎች ጥቃት ደርሶባቸዋል፡፡
ከፈረንጆቹ 2019 ጀምሮ ደቡብ ሱዳን መንግስትን ከዳርፉር፣ከሳውዝ ኮርዶፋንና ከብሉ ናይል አማጺዮች ጋር ለማደራደር ስትሰራ ቆይታለች፡፡