ሶሪያ ውስጥ በጅምላ መቃብሮች ቢያንስ 100 ሺ ሰዎች ሳይቀበሩ እንዳልቀሩ ተገለጸ
አሳድ ከ2011 ጀምሮ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሶሪያውያን ተገደልዋል ተብሎ ይገመታል
ለ24 አመታት የቆየው የአሳድ አስተዳደር አማጺያኑ በፈጸሙት የ12 ቀናት መብረቃዊ ጥቃት እንዲገረሰስ እና አሳድም ወደ ሩሲያ እንዲኮበልል ሆኗል
ሶሪያ ውስጥ በጅምላ መቃብሮች ቢያንስ 100 ሺ ሰዎች ሳይቀበሩ እንዳልቀሩ ተገለጸ።
መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው የሶሪያ የአድቮኬሲ ድርጅት በደማስቆ ከተማ በሚገኘው የጅምላ መቃብር በቀድሞው ፕሬዝደንት በሽር አል አሳድ የተገደሉ ቢያንስ 100 ሺ ሰዎች ተቀብረዋል ተብሎ እንደሚገመት በትናንትናው እለት አስታውቋል።
ሞአዝ ሞስጠፋ ለሮይተርስ ከደማስቆ በስልክ እንደተናገሩት ከደማስቆ በሰተሰሜን በኩል 40 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አል ቁጣይፋህ ማንነታቸው የማይታወቁ ሰዎች ለአመታት ከተቀበሩባቸው አምስት ቦታዎች አንዱ ነው።
"በትንሽ 100ሺ ሰዎች ተቀብረዋል ተብሎ ይገመታል" ሲል የሶሪያ የአደጋ ጊዜ ግብረ ኃይል ኃላፊው መስጠፋ ተናግሯል።
"ይህ በጣም፣ በጣም በጥንቃቄ የተቀመጠ ግምት ነው።"
ሙስጠፋ እንዳሉት ከሶሪያን ጎንለጎን የአሜሪካ እና የእንግሊዝ ዜጎች የተቀበሩባቸው ጅምላ መቃብሮች ከአምስት በላይ እንደሚሆኑ እርግጠኛ ናቸው። ሮይተርስ የሙስጠፋን መረጃ መረጃ ማረጋገጥ እንዳልቻለ ገልጿል።
አሳድ በተቃዋሚዎች ላይ ያደርሱ የነበረው ጥቃት ወደ አጠቃላይ የእርስበርስ ጦርነት ከተለወጠበት ከ2011 ጀምሮ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሶሪያውያን ተገደልዋል ተብሎ ይገመታል።
አሳድ አና በ2000 የሞቱት አባቱ ሀፌዝ በሶሪያውያን፣ በመብት ተቆርቋሪ ተቋማት እና በሌሎች መንግስታት በሀገሪቱ ባለው አደገኛ እስር ቤቶች ውስጥ ከህግ አግባብ ውጭ ግድያ በመፈጸምና በሌሎች ወንጀሎች ሲከሷቸው ቆይተዋል።ነገርግን አሳድ በተደጋጋሚ ይህን አስተባለብሏል።
ለ24 አመታት የቆየው የአሳድ አስተዳደር አማጺያኑ በፈጸሙት የ12 ቀናት መብረቃዊ ጥቃት እንዲገረሰስ እና አሳድም ወደ ሩሲያ እንዲኮበልል ሆኗል።
ምዕራባዊያን ሀገራት ሶሪያን ከተቆጣጠረው ሀያት ታህሪር አል ሻም ቡድን ጋር በሶሪያ መረጋጋት ስለሚፈጠርበት ሁኔታ እየተመካከሩ መሆናቸውን እየገለጹ ናቸው።