በአወዛጋቢ የዳኛ ውሳኔ ምክንያት በተነሳ ግጭት 135 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ
ይህ ችግር የተፈጠረው ለጊኒውለ ወታደራዊ ጁንታ መሪ ማማዲ ዶምቦያ ክብር በተዘጋጀ የፍጻሜ ጨዋታ ላይ ነው።
የሀገሪቱ መንግስት የሟቾች ቁጥር 56 እንደሆነ ይፋ አድርጎ ነበር
በአወዛጋቢ የዳኛ ውሳኔ ምክንያት በተነሳ ግጭት 135 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ።
በደቡብ ምስራቅ ጊኒ በሚገኝ የእግር ኳስ ስቴዲየም ውስጥ በተፈጠረ ትርምስ ምክንያት 135 ሰዎች መሞታቸውን ሮይተርስ የሀገሪቱን የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ቡድን ጠቅሶ ዘግቧል።
የሀገሪቱ መንግስት የሟቾች ቁጥር 56 እንደሆነ ይፋ አድርጎ ነበር።
ዳኛው ያሳለፉት አወዛጋቢ ውሳኔ በንዘረኮሬ በተካሄደው ጨዋታ ላይ ትርምስ እንዲነሳ እና ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ እንዲወረውር በማድረጉ ምክንያት ተመልካቶች ሊያመልጡ ሲሞክሩ ከባድ መረጋገጥ ተፈጥሯል።
ይህ ችግር የተፈጠረው ለጊኒውለ ወታደራዊ ጁንታ መሪ ማማዲ ዶምቦያ ክብር በተዘጋጀ የፍጻሜ ጨዋታ ላይ ነው።
በንዘረኮሪ የሚገኙ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ቡድን በትናንትናው እንደገለጸው የሟቾቹን ቁጥር ግምት ይፋ ያደረገው መረጃዎችን ከሆስፒታል፣ ከመቃብር ቦታዎች፣ ከመስጂድ፣ ከቤተክርስቲያን እና ከአካባቢው ሚዲያዎች በመሰብሰብ ነው።
"አሁን ላይ በስቴዲየሙ ውስጥ የሞቱ ሰዎች ቁጥር አብዛኞቹ ህጻናት የሆኑ 135 እንደሆነ እንገምታለን" ያለው ቡድኑ 50 ሰዎች እስካሁን ያሉበት አለመታወቁንም አክሎ ገልጿል።
ቡድኑ ለዚህ ችግር ከተመልካች ይልቅ ለባለስልጣናት ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት ያልተመጣጠነ ኃይል ተጠቅመዋል ያላቸውን የጸጥታ ኃይሎች ተጠያቂ አድርጓል።
ባለስልጣናትን እና ሌሎችን የያዙ ተሽካርካሪዎች በተጨናነቀው የስታዲየሙ በር በፍጥነት በሚወጡበት ወቅት ተመልካቶችን መግጨታቸውን ቡድኑ ገልጿል።
ባለፈው ሰኞ እለት በተፈጠረውን ክስተት ላይ ምርመራ እንደሚያደርግ የገለጸው መንግስት ቡድኑ ላወጣው መግለጫ ምላሽ አልሰጠም።