ፍሊስጤማውያን ነጻነታቸውንና ሉዓላዊ መንግስት የመመስረት መብታቸውን በአደባባይ ተዘርፈዋል- ሙሳ ፋኪ
ሰላምን ማረጋገጥ የሚቻለው ለመሰረታዊ መብቶች እውቅና በመስጠትና ፍትህን በማስፈን ብቻ ነው ብለዋል
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የዓለም ፍትህ ፍ/ቤት በእስራኤል ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ አድንቀዋል
የፍሊስጤም ህዝብ ነጻነታቸውንና ሉዓላዊ መንግስት የመመስረት መብታቸውን በስም በሌለው ጦርት አደባባይ ተዘርፈዋል ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንብር ሙሳ ፋኪ መሃመት አስታወቁ።
44ኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንብር ሙሳ ፋኪ መሃመት በስብሰባው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ በአፍሪካ እና በዓለም ዙሪያ ያሉ ስጋቶቸ በየእለቱ እየጨመሩ መምጣታቸውን አስታውቀዋል።
አፍሪካ እንዲሁም ዓለም እያስተናገደች ያለውን አለመግባባቶች እና ጭካኔ የተሞላባቸው ግጭቶች መፍታት የሚቻለው በንግግር እና በመግባባት ብቻ እንደሆነም ሊቀ መንበሩ ገልጸዋል።
ሙሳ ፋኪ በንግግራቸው ስለ ፍሊስጤም እስራኤል ጦርነት ያነሱ ሲሆን፤ “የፍሊስጤም ህዝብ በታሪከ ውስጥ ስም በሌለው አጥፊ ጦርነት ነጻነታቸውንና ሉዓላዊ መንግስት የመመስረት መብታቸውን አይናችን ስር አደባባይ ላይ ተዘርፈዋል” ብለዋል።
“በጦርነቱ ተነግሮ የማያልቅ ጭካኔ የተሞላበት ተግባራት ተፈጽሟል” ያሉት ሊቀ መንበሩ፤ “ጦርነቱ እንዲቆም፣ ሁሉም ታጋቾች እና እስረኞች እንዲፈቱ ቀደም ብለን ጥሪ ቅርበን ነበር” ብለዋል።
የፍልስጤም እና የእስራኤል ህዝቦች እንዲሁም በመካለኛው ምስራቅ ክልል ያሉ ህዝቦች ደህንነታው ተጠብቆ እንዲኖሩ የሁለት መንግስታት መርህ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ መፍትሄ ለማምጣት ቁርጠኝነት መስራት እንደሚያስፈልግ እና ዓለም አቀፍ ህግን በማክበር ተገቢ እንደሆነም አሳስበዋል።
ሰላም እና ደህንነት ማስጠበቅ የሚቻለው ፍህን በማስፈን እና ለሁሉም መሰረታዊ መብቶች እውቅና በመስጠት ብቻ እንደሆነም አስታውቀዋል።
ሊቀ መንበሩ ሙሳ ፋኪ በንግግራቸው አክለውም የዓለም የፍትህ ፍርድ ቤት ከሰሞኑ በእስራኤል ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ እደሚያደንቁም አስታውቀዋል።
ደቡብ አፍሪካ የፍሊስጤምን ጉዳይ ወደ ዓለም ፍርድ ቤት በመውሰድ እና በእስራኤል ላይ በማስወሰን ላሳየችው ቁርጠኝነትም ሊቀ መንበሩ በጉባዔው ፊት ሀገሪቱን አመስግነዋል።
ደቡብ አፍሪካ ከዚህ ቀደም “እስራኤል በጋዛ በሚኖሩ ፍሊስጤማውያን ላይ የዘር ፍጅት እየፈጸመች ነው” በማት ሀገሪቱንም በዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት መክሰሷ ይታወሳል።
በሀገራት መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን የሚያስተናግደው ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ከሃማስ ታጣቂዎች ጋር ጦርነት በምታደርግበት ወቅት የዘር ማጥፋት ድርጊቶችን ለመከላከል እርምጃ እንድትወስድ ብይን መስጠቱም ይታወሳል።