የአፍሪካ ህብረት በኒጀር በተፈጸመው መፈንቅለ መንግስት ምክንያት ሀገሪቱን አግዷል፤ ማዕቀብ ለመጣል እየተዘጋጀ መሆኑን ገልጿል
የአፍሪካ ህብረት በኒጀር በተፈጸመው መፈንቅለ መንግስት ምክንያት ሀገሪቱን አግዷል፤ ማዕቀብ ለመጣል እየተዘጋጀ መሆኑን ገልጿል።
የአፍሪካ ህብረት በኒጀር መፈንቅለ መንግስት ከተካሄደ ከፈረንጆቹ ሐምሌ 26 ጀምሮ ሀገሪቱን ከሁሉም እንቅስቃሴዎች ማገዱ እና ስልጣን የተቆናጠጠው ጁንታ ኘሬዝደንት መሀመድ ባዙምን ወደ ቦታቸው እንዲመልሳቸው ማሳሰቡ ይታወሳል።
የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ጸጥታ ምክርቤት የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ጥምረት የሆነው ኢኮዋስ ሊያደገው የሚችለውን ወደታደራዊ እርምጃ ጉዳይ እንደሚያውቀው እና ሀይል መላክ የሚያመጣውን አንደምታ እንዲያጤነው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽንን ጠይቀናል ብሏል።
ኢኮዋስ በኒጀር ዲሞክራሲ ስርአትን ለመመለስ የሚደረገው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ውድቅ የሚሆን ከሆነ ወታደር ሊያሰማሩ እንደሚችሉ እየገለጹ ናቸው።
የአፍሪካ ህብረት፣ አባል ሀገራት እና አለምአቀፍ ማህበረሰብ በኒጀር ያለውን ጉዳይ ከማባባስ እንዲቆጠብ ጠይቀዋል።
ህብረቱ ከአፍሪካ ውጭ ሊደረግ የሚችልን ጣልቃ ገብነት እንደማይቀበል ገልጿል።
የኢኮዋስ አባል ሀገራት ወታደራዊ ኃላፊዎች በቅርቡ ስብሰባ ካደረጉ በኋላ ይፋ እንዳደረጉት በኒጀር ጣልቃሊገቡ የሚችሉበት ሚስጥራዊ ቀነገደብ አስቀምጠዋል።