ኬንያን በቀጣዮቹ አምስት ዓመታ ለመምራት አራት እጩዎች ቀርበዋል
ካ ህብረት የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን የሚታዘብ ልዑክ አሰማራ፡፡ተጠባቂው የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ 32 ቀናት ብቻ ቀርተውታል፡፡
የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ነሀሴ 2 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚካሄድ የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ጊዜ ሰሌዳ ያስረዳል፡፡ በምርጫው ላይ ለ5ኛ ጊዜ እጩ የሆኑት ራይላ ኦዲንጋ እና ዊሊያም ሩቶ ዋነኛ ተፎካካሪ ናቸው
የአፍሪካ ህብረትም በአባል ሀገራቱ የሚካሄዱ ምርጫዎችን የሚታዘብ ሲሆን የዘንድሮውን የኬንያ ጠቅላላ ምርጫ ለመታዘብ ስምንት ቡድን ያለው የምርጫ ታዛቢ ልዑክ መላኩን በድረገጹ አስታውቋል፡፡
ይህ የምርጫ ልኡክ ከምርጫ ቅድመ ዝግጅት እስከ ድህረ ምርጫ ወቅቶች ድረስ ያሉ ስራዎችን በመታዘብ ሪፖርት እንዲያቀርብ ተልዕኮ ተሰጥቶታል ተብሏል፡፡
ኬንያን በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ለመምራት እጩ ፕሬዝዳንቶች በምረጡኝ ቅስቀሳ ላይ ሲሆኑ አሁን ላይ ፉክክሩ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡
ኬንያን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት አራት እጩዎች ቀርበው በምርጫ ቅስቀሳ ላይ ካሉት እጩ ፕሬዝዳንቶች መካከል ባለፉት ምርጫዎች ላይ ለአራት ጊዜ ተወዳድረው ሽንፈትን ያስተናገዱት የኦሬንጅ ዲሞክራቲክ ሙቭመንቱ ራይላ ኦዲንጋ ዋነኛው ተፎካካሪ ናቸው፡፡
ራይላ ኦዲንጋ በፈረንጆቹ 1997 ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀገራቸውን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት እጩ የነበሩ ሲሆን በምርጫው ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡
በነዳጅ እና ሀይል ልማት ዘርፍ ነጋዴ የሖኑት የ77 ዓመቱ ኦዲንጋ ላለፉት አራት ተከታታይ ፕሬዝዳንታዊ የምርጫ ወቅቶች ላይ እጩ ቢሆኑም አብላጫ የህዝብ ድምጽ ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡
ውጤታቸውን ተከትሎም ራይላ ኦዲንጋ ከፕሬዝዳናታዊ ምርጫ ራሳቸውን ማግለላቸውን ከአምስት ዓመት በፊት ቢናገሩም ዘግይተው በሰጡት መግለጫ ለአምስተኛ ጊዜ ለፕሬዝዳንትነት መልሰው እንደሚወዳደሩ አሳውቀዋል፡፡
ኬንያን አሁን ላይ በምክትል ፕሬዝዳንትነት እያገለገሉ ያሉት የዲሞክራቲክ ዩኒየኑ ዊሊያም ሩቶ ሌላኛው ዋነኛ ተፎካካሪ ናቸው፡፡