ሰኞ ጀነራል ብሪክ ኦሊጉ ንጉማ ቃለ መሀላ ይፈጽማሉ ተብሏል
የአፍሪካ ህብረት የመንግስት ግልበጣ የተደረገባትን ጋቦን ከአባልነት አግዷል።
ይህም ከ2020 ወዲህ ስምንተኛ መፈንቅለ መንግስት በተደረገባት ሀገር የተወሰደ የመጀመሪያ እርምጃ ሆኗል።
መንግስት ግልበጣው የቦንጎ ቤተሰብን የስድስት አስርት ዓመታት የስልጣን ቆይታ እንዲያከትም አድርጓል።
በቀጠናው መንግስት ፈንቅለው ስልጣን እንደያዙ ጁንታ ሁሉ የጋቦን ወታደራዊ መንግስትም ስልጣኑን ማጠናገር ይፈልጋል፤ ምንም እንኳ ዓለም አቀፍ ውግዘት ቢበረታበትም።
በሚቀጥለው ሰኞ የመፈንቅለ መንግስቱ አቀናባሪ ጀነራል ብሪክ ኦሊጉ ንጉማ ቃለ መሀላ ይፈጽማሉ ተብሏል።
የአፍሪካ ህብረት የሰላምና ደህንነት ም/ቤት ሀሙስ የመጀመሪያ እርምጃ በመውሰድ፤ ጋቦንን ህገ-መንግስታዊ ስርዓትን እስክትመልስ ድረስ ከህብረቱን እንቅስቃሴና ተሳትፎ አግዷታል።
ጋቦንን በአባልነት የያዘው የማዕከላዊ አፍሪካ የፖለቲካ ጥምረትም የመንግስት ግልበጣውን አውግዟል።
ጥምረቱ ምላሽ ለመስጠትም አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱን አስታውቋል፤ ምንም እንኳ የቆረጠውን ቀን ባያሳውቅም።
መንግስት ገልባጮች የጋቦን የምርጫ ውጤት በታወጀ በደቂቃዎች ልዩነት ስልጣን መቆጣጠራቸውን ረቡዕ ሌሊት አሳውቀዋል።