ህብረቱ በፖሊዮ በተጠቁ የማላዊ አካባቢዎች ላይ የአደጋ ጊዜ ምላሽ እርምጃዎችን እንደሚወስድ አስታወቀ
የማላዊ መንግስት ወረርሺኙን ለመቆጣጠር የአደጋ ጊዜ ኦፕሬሽን ኮሚቴ ማቋቋሙን ገልጿል
በማላዊዋ መዲና ሊሎንግዌ የፖሊዮ በሽታ እንደተከሰተ የዓለም ጤና ድርጅት ማስታወቁ ይታወሳል
በማላዊ በፖሊዮ በተጠቁ አካባቢዎች የአደጋ ጊዜ ምላሽ ለመስጠት እና በቀጣይም የወረርሽኙን የድጋፍ እቅድ ለማዘጋጀት በዝግጅት ላይ መሆኑን የአፍሪካ ህብረት አስታወቀ።
ህብረቱ ይህንን ያለው የማላዊ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሃሙስ ዕለት አንድ የተረጋገጠ የፖሊዮማይላይትስ (ፖሊዮ) መከሰቱን ከዘገበ በኋላ ነው።
ወረርሽኙ መከሰቱን ተከትሎ የማላዊ መንግስት የአደጋ ጊዜ ግምገማ እና ሁኔታዊ ትንተና በማካሄድ የአደጋ ጊዜ ኦፕሬሽን ኮሚቴን እንደሚያንቀሳቅስ ከቀናት በፊት ተናግሮ ነበር።
በዚህም የአፍሪካ ህብረት በአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል (አፍሪካ ሲዲሲ) ጉዳዩን በቅርበት እንደሚከታተል እና እንደ አስፈላጊነቱ ተጨማሪ የአደጋ ጊዜ ምላሽ ድጋፍ ለማድረግ ከማላዊ መንግስት ጋር እንደሚሰራ አስታውቋል።
"የአፍሪካ ሲዲሲ በማላዊ በተጎዱ ወረዳዎች ላይ የአደጋ ምላሽ እርምጃዎችን ለመውሰድ በዝግጅት ላይ ነው"ም ብለዋል የአፍሪካ ህብረት በትናንትናው እለት ባወጣው መግለጫ፡፡
በማላዊዋ መዲና ሊሎንግዌ የፖሊዮ በሽታ እንደተከሰተ የዓለም ጤና ድርጅት ማስታወቁ ይታወሳል።