ኢትዮጵያ ተፈጽሟል የተባለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ለማጣራት ከህብረቱ ጋር ለመስራት መዘጋጀቷ የሚደነቅ ነው- አፍሪካ ህብረት
የአብረን እንስራ ሀሳቡ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ እንደመጣ የአፍሪካ ህብርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ መሀማት ገለፁ
ኢትዮጵያ ተፈጸሙ የተባሉትን የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ከአፍሪካ ህብረት ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በጋራ እንዲያጣሩ ጥሪ ማቅረቧ ይታወሳል
በትግራይ ክልል ተፈጽሟል የተባለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ለማጠራት በሚደረገው ጥረት የኢትዮጵያ መንግስት ከአፍሪካ ህብረት ጋር በትብብር ለመስራት ያሳየውን ዝግጁነት እንደምያደንቁ የህብረቱ ኮምሽነር ሙሳ ፋኪ መሀማት ገለጹ፡፡
ኮሚሽነሩ ይህን ያሉት ዛሬ በትግራይ ክልል የሚደረገው ምርመራን በማስመለከት የአፍሪካ ኮሚሽን የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ተሳትፎ በምን አግባብ መሆን አለበት በሚል አጀንዳ ዙርያ፤ ከኢትዮጵያው ም/ጠ/ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በመከሩበት ወቅት ነው፡፡
ተፈፀመ ስለተባለው ወንጀል ለማጣራት በሚደረገው ምርመራ ከህብረቱ ጋር በትብብር እንዲሰራ መጀመርያ ሀሳቡ የመጣው ከቀናት በፊት መጋቢት 9/2013 ዓ.ም የህብረቱ የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ ፤ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) መሆኑንም የአፍሪካ ኮሚሽነሩ ሙሳ ፋኪ መሀማት ገልጸዋል፡፡
በህብረቱ ድህረ-ገጽ የወጣው ጽሁፍ እንደሚያመላክተው ከሆነ ኢትዮጵያ ተፈጸመ የተባለውን ወንጀል ለማጣራት ከህብረቱ ጋር ለመስራት ያሳየችው ዝግጁነት የሚደነቅ ነው ብለዋል ኮሚሽነሩ ሙሳ ፋኪ መሀማት፡፡
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትግራይ ክልል በተካሄደው “የሕግ ማስከበር ዘመቻ” የመብት ጥሰት ተፈጽሟል በሚል ለሚቀርብ ቅሬታ የአፍሪካ የሰብዓዊ እና የሰዎች መብቶች ኮሚሽን ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር ሆኖ እንዲያጣራ መፍቀዳቸውን አስታወቁ፡፡