ኢኮኖሚ
አውስትራሊያ የብሪታንያ ንጉሳዊ አገዛዝን ምስል ከባንክ ኖቷ ልታስወግድ ነው
የአምስት ዶላር ኖት የሀገሪቱን ባህልና ነባር ህዝብ በሚያከብር አዲስ ንድፍ ይተካል ተብሏል
አውስትራሊያ ለመጨረሻ ጊዜ በአምስት ዶላር ገንዘቧ ላይ ለውጥ ያደረገችው በፈረንጆቹ በ2016 ነበር
አውስትራሊያ የብሪታንያ ንጉሳዊ አገዛዝን ምስል ከባንክ ኖቷ ልታስወግድ ነው
አውስትራሊያ የብሪታንያ ንጉሳዊ አገዛዝ ምስሎች በገንዘብ ኖቶች ላይ መታተማቸው እንደማይቀጥል ተናግራለች።
በእርምጃው ሀገሪቱ በአዲሱ የአምስት ዶላር ገንዘቧ ላይ የንጉስ ቻርለስ ሳልሳዊ ምስል እንደማይኖር አስታውቃለች።
የአውስትራሊያ ማዕከላዊ ባንክ እንዳስታወቀው የቀደመው የንግስት ኤልዛቤት ምስል የሀገሪቱን ባህልና ነባር ህዝብ በሚያከብር አዲስ ንድፍ ይተካል።
ባንኩ ውሳኔው "የመጀመሪያዎቹ አውስትራሊያውያንን ባህል እና ታሪክ" ለማክበር ያለመ ነው ብሏል።
ባንኩ በመግለጫው "የአምስት ዶላር ኖት ሌላኛው ጎን የአውስትራሊያን ፓርላማ ማቅረቡን ይቀጥላል" ብሏል።
አምስት ዶላር በአሁኑ ጊዜ የእንግሊዝ ንጉሳዊ አገዛዝ አባልን የሚያሳይ የአውስትራሊያ ብቸኛ የባንክ ኖት ነው።
ሆኖም አሁንም ንጉስ ቻርልስ በአውስትራሊያ ሳንቲሞች ላይ እንደሚታይ ይጠበቃል።
አሁን ያለው አምስት ዶላር አዲሱ ዲዛይን እስኪተካ ድረስ ዝውውሩ ይቀጥላል መባሉን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሀገሪቱ ለመጨረሻ ጊዜ በአምስት ዶላር ገንዘቧ ላይ ለውጥ ያደረገችው በፈረንጆቹ 2016 ነበር።