በጥገኛ ተውሳክ ምክንያት የህልውና ስጋት የተጋረጠባቸው በርካታ የአውስትራሊያ ንቦች “በለይቶ ማቆያ”ናቸው ተባለ
በአውስትራሊያ ንቦች ላይ አደጋ የደቀነው ጥገኛ ተውሳክ ”ቨሮዋ”በመባል ሚታወቅ ተባይ ነው ተብሏል
“ቨሮዋ” አሁን ባለበት ፍጥነት መስፋፋቱ ከቀጠለ አውስትራሊያ እስከ 70 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ ያጋጥማታል ተብሏል
በጥገኛ ተውሳክ ምክንያት የህልውና ስጋት የተጋረጠባቸው በርካታ የአውስትራሊያ ንቦች “በለይቶ ማቆያ” መሆናቸው ተገለጸ፡፡
በአውስትራሊያ ንቦች ላይ አደጋ የደቀነው ጥገኛ ተውሳክ ”ቨሮዋ” በመባል ሚታወቅ ሲሆን ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በሲድኒ መታየቱ ተገልጿል፡፡“ቨሮዋ” በአውስትራሊያ የማር ገበያ ላይ በሚሊዮን ዶላሮች የሚገመት ኪሳራ እንደሚያደርስም ከወዲሁ ተገምቷል፡፡
በዚህም ከፍተኛ ስጋት ላይ የወደቁ የአውስትራያ የማር ነጋዴዎች የንብ ቀፎዎቻቸው እንዳያንቀሳቅሱ ተከልክለዋል፡፡
አውስትራሊያ እስከሁን ጸረ ንብ የሆነ መሰል በጥገኛ ተውሳክ ያልነበራት ብቸኛ አህጉር እንደነበረች ይታወቃል፡፡
“ቨሮዋ” የተሰኘው ጥገኛ ተውሳክ ወደ ንቦች ቀፎ በመግባት በሽታ የሚያስተላለፍና ንቦችን የሚገድል ተባይ ነው፡፡አሁን ላይ “ቨሮዋ” በአውስትራሊያ ኒው ሳውዝ ዌልስ አከባቢ የታ ሲሆን፤ ሀገሪቱ ባለስልጣናት ስርጭቱን ለመግታት የተለያዩ አርምጃዎች በመውሰድ ላይ ናቸው፡፡
በዚህም ጥገኛ ተውሳክ በታየበት አከባቢ 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ የንብ ቆፎ እንዲወድም (ከጥቅም ውጭ እንዲሆን) የተወሰ ሲሆን እስካሁን 400 የንብ ቀፎዎች ከጥቅም ውጭ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ተባዮቹ ከታዩበት 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙ ሁሉም ቀፎዎች ላይ ጥብቅ ክትትል እንዲደረግ የአውስትራሊያ የእንስሳትና አከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡
በሌላ በኩል “በለይቶ ማቆያ” እንዲቆዩ የተደረጉት ንቦች ያሉባቸው ቀፎዎች ወደየትኛውም ቦታ እንዳይነቀሳቀሱ ተደርጓል፡፡
“ቨሮዋ” አሁን ባለበት ፍጥነት መስፋፋቱ ከቀጠለ፤ ሀገሪቱ እስከ 70 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ ሊያጋጥማት እንደሚችል ጥናቶች አመላክተዋል፡፡አውስታራሊያ ከንብ የምታገኛቸው ውጤቶች ለምግብነት የምትጠቀምባቸው ምርቶችን 1/3ኛ እንደሚሸፍን ይነገራል፡፡