በአውስትራሊያ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአንድ ጊዜ ቻርጅ 1000 ኪ.ሜ የሚጓዝ መኪና ሰሩ
በፀሃይ ኃይል የሚሰራው ተሸከርካሪው ያለማቋረጥ ለ12 ሰዓት መጓዝ ችሏል
“ዘ ስዊፍት 7” የሚል መጠሪያ የተሰጠው መኪናው አዲስ የዓለም ክብረወሰን መስበሩም ተነግሯል
የአውስትራሊያ ተማሪዎች በፀሃይ ኃይል እና በኤሌክትሪክ መኪና ታሪክ አዲስ ከብረ ወሰን ማስመዝገባቸው ተነግሯል።
የአውስትራሊያ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሰሩት አዲሱ መኪና ያለ ማቋረጥ ለ12 ሰዓታት 1000 ኪሎ ሜትር መጓዝ መቻሉም ተነግሯል።
“ዘ ስዊፍት 7” የሚል መጠሪያ የተሰጠው መኪናው በኒው ሳውዝ ዌልስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተሰራ መሆኑም ተነግሯል።
መኪናው በሰዓት 85 ኪሎ ሜትር ገደማ መጓዝ የሚችል ሲሆን፤ ይህም በአንድ ጊዜ ቻርጅ ከ1000 ኪሎ ሜትር በላይ መጓዝ የቻለ ፈጣኑ የኤሌክትሪክ መኪና አስብሎታል።
በዚህም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሰሩት መኪና በአዲስ ክብረ ወሰን የሆነ ርቀት ተጉዟል የተባለ ሲሆን፤ ፍጥነቱ ከተረጋገጠ በኋላ የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ እንደሚሰፍርም ተነግሯል።
በኒው ሳውዝ ዌልስ ዩኒቨርሲቲ የመካኒካል ኢንጂነሪንግ ተማሪ የሆነው የስዊፍት ፕሮጄክት ቡድን መሪ የዓለም ምርጥ የተባለን ነገር መስራት በመቻል የተለየ ስሜት አለው ብሏል።
“መኪናውን መስራት በጀመርንበት ከ2 ዓመት በፊት ሁሉም ነገር በኮሮና ምክንያት የተዘጋጋበት እና አስቸጋሪ ወቅት ነበር” ያለው ተማሪው፤ “በርካታ ሰዓታትንን በሰራ አሳልፈናል፤ ዋጋም አግኝተንበታል” ሲል ተናግሯል።