የአውስትራሊያ የኦርቶዶክስ ጳጳስ በስለት ጥቃት ለፈጸመባቸው ግለሰብ “ይቅርታ አድርጊያለሁ” አሉ
አቡነ ማር ማሪ ኢማኑኤል በቀጥታ በሚተላለፍ መርሃ ግብር ላይ እያስተማሩ ነበር ጥቃት የተፈጸመባቸው
ጳጳሱ “ይህንን ጥቃት እንዲፈጽም ለላኩትም ይሁን ጥቃቱን ለፈጸመው ግለሰብ ሁሌም እጸልያለሁ” ብለዋል
በአውስትራሊያ ሲድኒ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በማተማር ላይ እያሉ በስለት ጥቃት የተፈጸመባቸው የኦርቶዶክስ ጳጳስ አቡነ ማር ማሪ ኢማኑኤል ጥቃቱን ላደረስ ግለሰብ ይቅርታ ማድረጋቸውን አስታወቁ።
ባሳለፍነው ሰኞ አውስትራሊያ ሲድኒ ከተማ ዳርቻ በሚገኝ 'ቤተ ክርስቲያን' ውስጥ በተፈጸመ በስለት የመወጋት አደጋ አቡነ ማር ማሪ ኢማኑኤል በርካቶች መቁሰላቸውን ፖሊስ መግጹ ይታወሳል።
ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት አቡነ ማር ማሪ ኢማኑኤል በአውስትራሊያ ሲድኒ ከተማ በቀጥታ በሚተላለፍ ሰብከት ላይ እንደነበሩም ይታወቃል።
ታዲያ በዚህ ወቅት ስለት ያዘ አንድ ታዳጊ ወደ ቤተክርስቲያኑ በመግባ በማስተማር ላይ የነበሩትን ጻጻስ በስለት የወጋ ሲሆን፤ ሌሎች ሰዎችንም ማቁሰሉ ይታወሳል።
ጥቃቱን ተከትሎም ሰዎች በቤተክርስቲያኒቱ አቅራቢያ ከተሰበሰቡ በኋላ አለመረጋጋቶች ተከስተው እንደነበረም ነው የተነገረው።
ፖሊስ ጥቃቱ ያደረሰውን የ16 ዓመት ታዳጊ መያዙን እና ለምርመራ ተባባሪ መሆኑን አስታውቋል።
ከጥቃቱ የተረፉት የአውስትራሊያ የኦርቶዶክስ ጳጳስ አቡነ ማር ማሪ ኢማኑኤል ለመጀመሪያ ጊዜ በድምጽ ባስተላለፉት መልእክት በፍጥነት እያገገሙ መሆኑን እና በመልካ ጤንነት ለይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።
አቡነ ማር ማሪ ኢማኑኤል በመልእክታቸውም “ማንም ይሁን ማን ይህንን ላደረገው ግለሰብ ይቅርታ አድርጌያለሁ” ማለታቸውም በድምጽ ባስተላለፉት መልእክት ተሰምቷል።
“ይህንን ጥቃት እንዲፈጽም ለላኩትም ይሁን ጥቃቱን ለፈጸመው ግለሰብ ሁሌም ጸሎት አደርጋለሁ” ያሉት ጳጳሱ፤ “በታላቁ ኢየሱስ ስም ይቅርታ አድርጌላቸዋለሁ” ብለዋል።
አቡነ ማር ማሪ ኢማኑኤል በተቀረጸ ድምጽ ባስተላለፉት መልዕክት ህብረተሰቡ እንዲረጋጋም እና ከፖሊስ ጋር እንዲተባርም ጥሪ አቅርበዋል።
የ53 ዓመቱ አቡነ ማር ማሪ ኢማኑዔል የአሲሪያን ኦርቶዶክስ ክራይስት ዘ ጉድ ሼፐርድ የተባለው ቤተ-ክርስቲያን በፈረንጆቹ 2009 ቄስ፤ ቀጥሎ ደግሞ በ2011 አቡን ሆነው ሲመት ተቀብለዋል።
አቡነ ማር ማሪ ኢማኑዔል የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን እንዲሁም ፆታቸውን ስለሚቀይሩ ሰዎች “በፈጣ ዘንድ ወንጀል ነው” በማለት በግልጽ በመተቸት እና በመቃወም ይታወቃሉ።