በአውስትራሊያ ሲድኒ በሚገኝ ቤተክርስቲያን ውስጥ በርካቶች በስለት ተወጉ
በማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቀው ቪዲዮ ቢለዋ የያዘው ግለሰብ መድረክ ላይ የነበረውን አገልጋይ ጎትቶ ሲወጋው ይታያል
በሰዎች ላይ የደረሰው ጉዳት ለህይወት አስጊ አለመሆኑን እና ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ፖሊስ ገልጿል
በአውስትራሊያ ሲድኒ ከተማ በሚገኝ ቤተክርስቲያን ውስጥ በርካቶች በስለት ተወጉ።
አውስትራሊያ ሲድኒ ከተማ ዳርቻ በሚገኝ ቤተክርስቲያን ውስጥ በተፈጸመ በስለት የመወጋት አደጋ በርካቶች መቁሰላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
ፖሊስ ይህን ጥቃት አድራሽ መያዙን እና ለምርመራ ተባባሪ መሆኑን የፖሊስ ቃል አቀባይን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።
ይህ ጥቃት ከሴንትራል ቢዝነስ ዲስሪክት በስተምዕራብ በኩል በምትገኘው ዌክሌይ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ የተፈጸመ ነው።
በሲድኒ በሚገኝ የገበያ አዳራሽ ውስጥ ስድስት ሰዎች በቢለዋ ተወግተው ከተገደሉ በኋላ በሶስት ቀናት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የተፈጸመ ጥቃት ነው ተብሏል።
የዛሬው አደጋ የተከሰተው ዌክሌይ ውስጥ የሚገኘው 'ክሪስት ዘ ጉድ ሸፐርድ ቸርች' አገልግሎት እየሰጠ ባለበት ወቅት ሲሆን ፖሊስ በቦታው የተሰበሰበውን ህዝብ ለመቆጣጠር እስካሁን በቦታው እንደማገኝ ተዘግቧል።
በሰዎች ላይ የደረሰው ጉዳት ለህይወት አስጊ አለመሆኑን እና ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።
በአደጋው የቸርቹ መሪ እና በርካታ ምዕመናን ጉዳት ደርሶባቸዋል። በማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቀው ቪዲዮ ቢለዋ የያዘው ግለሰብ መድረክ ላይ የነበረውን አገልጋይ ጎትቶ ሲወጋው ይታያል።