ከውሽማው ጋር ለማሳለፍ ሲል ለሚስቱ ታግቻለሁ ያለው ሰው 16 ሺህ ዶላር ካሳ እንዲከፍል ተፈረደበት
ሚስት ባሏ የምር የታገተ መስሏት ጉዳዩን ለፖሊስ ማመልከቷን ተከትሎ እገታው የውሸት መሆኑ ተረጋግጧል
ፖሊስም ላባከነው ጊዜ 16 ሺህ ዶላር እንዲከፈለው ጠይቋል
ከውሽማው ጋር ለማሳለፍ ሲል ለሚስቱ ታግቻለሁ ያለው ሰው 16 ሺህ ዶላር ካሳ እንዲከፍል ተፈረደበት።
የ35 ዓመቱ ፖል ሊራ አውስትራሊያዊ ሲሆን ባለትዳርም ነው።
ግለሰቡ ከውሽማው ጋር ለመዝናናት ሲል ለሚስቱ ባልታወቁ ሰዎች እንደታገተ የጽሁፍ መልዕክት እንዲደርሳት ያደርጋል።
ከዚህ በተጨማሪም ይህ ግለሰብ በመልዕክቱ ጉዳዩን ለፖሊስ እንዳትናገር ያስጠነቀቀ ቢሆንም ሚስት ግን ለባሏ ደህንነት ስትል ለፖሊስ ማመልከቷ ተገልጿል።
ጥቆማ የደረሰው ፖሊስም ባደረገው ክትትል ፖል ሊራ ታግቶ ሳይሆን ከውሽማው ጋር ለመዝናናት ሲል የፈጠረው ምክንያት መሆኑን ደርሶበታል።
ግለሰቡ ሳይታገት በሀሰት ታግቻለሁ በሚል ከትዳር አጋሩ ውጪ የዝሙት ወንጀል ከመፈጸሙ ባለፈ የፖሊስን ጉልበት፣ ጊዜ እና ሀብት ያላግባብ እንዲባክን አድርጓል በሚል ክስ ተመስርቶበታል።
ይህ አውስትራሊያዊ በፈጸማቸው ወንጀሎች የሰባት ዓመት እስር የተፈረደበት ሲሆን ለፖሊስም 16 ሺህ ዶላር እንዲከፍል ተፈርዶበታል ሲል ሲኤንኤን ዘግቧል።
እንዲሁም የሶስት ዓመት ማህበራዊ አገልግሎት እንዲሰጥም ተፈርዶበታልም ብለዋል።