ቻይና ከሩሲያ ጋር ባላት ቅርበት ምክንያት የሚደርስን ጫና እንደማትቀበል ገለጸች
አሜሪካ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ለምታደርሰው የበላይነት ቻይና ሀላፊነቱን ትወስዳለች ስትል አስጠንቅቃለች
የሩሲያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጊ ላቭሮቭ ቻይናን በመጎብኘት ላይ ናቸው
ቻይና ከሩሲያ ጋር ባላት ቅርበት ምክንያት የሚደርስን ጫና እንደማትቀበል ገለጸች፡፡
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጊ ላቭሮቭ ወደ ቤጂንግ አቅንተው ከቻይና ፕሬዝዳንት እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ጋር መክረዋል፡፡
አሜሪካ የሰርጊ ላቭሮቭን የቤጂንግ ጉብኝት አስመልክቶ ባወጣችው መግለጫ የሞስኮ እና ቤጂንግ ትብብር ምክንያት ሩሲያ በዩክሬን ላይ የበላይነትን ከወሰደች ቻይና ሀላፊነቱን ትወስዳለች ስትል አስታውቃለች፡፡
የአሜሪካ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኩርት ካምቤል እንዳሉት የአውሮፓ ደህንነት ከምንም በላይ የሚያሳስበን ጉዳይ ነው፣ ሩሲያ በዩክሬን የጀመረችው አዲስ ጥቃት የአውሮፓን ሚዛን የሚያስት ነውም ብለዋል፡፡
ቻይና ለሩሲያ የምታደርገው ድጋፍ ከአሜሪካ ጋር ያላትን ወዳጅነት ይጎዳል፣ ይህ ሲሆን ደግሞ ዝም ብለን አናይም ሩሲያ በዩክሬን ለምታደርገው ጉዳት ቻይና ሀላፊነቱን ትወስዳለች ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡
የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአሜሪካ መግለጫ ዙሪያ በሰጠው ምላሽ ቤጂንግ ከሞስኮ ጋር በሚኖራት ግንኙነት ዙሪያ የማንንም ጫና አትቀበልም ብላለች፡፡
ቻይና እና ሩሲያ ኢኮኖሚ እና ንግድ ግንኙነታቸውን የማሳደግ መብት አላቸው፣ ይህን መሰል ግንኙነት የማንንም ጣልቃ ገብነትን አይፈልግም ስትልም ቻይና ምላሽ ሰጥታለች፡፡
ሩሲያ በየካቲት 2022 በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ከከፈተች በኋላ 20 በመቶ የዩክሬን ግዛቶችን ተቆጣጥራለች፡፡
አሜሪካ ለዩክሬን ከ5 ሺህ በላይ ክላሽ የተሰኘ የጦር መሳሪያ ሰጠች
ሩሲያ ጦሯን ወደ ዩክሬን ስትልክ "ልዩ ወታራዊ ዘመቻ" እያካሄደች መሆኑን ስትገልጽ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ምዕራባውያን እየተሳተፉ በመሆናቸው ግጭቱን ጦርነት ብላ እየጠራችው ነው።
አራት የዩክሬን ምስራቃዊ ግዛቶችን በከፊል የያዘችው ሩሲያ ሙሉ በሙሉ እስከምትቆጣጠራቸው ድረስ ማጥቃቷን እንደምትቀጥል መግለጿ ይታወሳል።
በቅረቡ ወሳኝ የተባለችውን አቭዲቪካን ጨምሮ በርካታ መንደሮችን የተቀጣጠረችው ሩሲያ ወደፊት ለመግፋት ጥረት እያደረገች ትገኛለች።