ስሙን "ትራምፕ" ወደሚል መጠሪያ የቀየረው ፖለቲከኛ
በአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የተነቃቃው አውስትራሊያዊ ፖለቲከኛ ስሙን ህጋዊ በሆነ መንገድ "አውሴ ትራምፕ" ወደሚል አስቀይሯል

ፖለቲከኛው ይህን ያደረገው ሀገሪቱን እየመራ ያለውን የማዕከላዊ-ግራ ዘመም ሌበር ፓርቲን ለመቃወም ነው ብሏል
በአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የተነቃቃው አውስትራሊያዊ ፖለቲከኛ ስሙን ህጋዊ በሆነ መንገድ "አውሴ ትራምፕ" ወደሚል ቀይሮታል።
ፖለቲከኛው ይህን ያደረገው ሀገሪቱን እየመራ ያለውን የማዕከላዊ-ግራ ዘመም ሌበር ፓርቲን ለመቃወም ነው ብሏል።
የሌበር ፓርቲ አብላጫ ወንበር በተቆጣጠረበት በምዕራብ አውስትራሊያ የላይኛው ምክርቤት የግል ተወዳዳሪ የሆኑት ቤን ዳውኪንስ አሁን ላይ በምክር ቤቱ ፓርላማ ጽረ ገጽ "አውሲ ትራምፕ" ተብለው ተዘርዝረዋል።
ፖለቲከኛው በኤክስ ገጹ ላይ ያለውን ስሙንም "የተከበሩ አውሴ ትራምፕ ኤምኤልሲ" በሚል ቀይሮታል።
"ጨካኝና ስልታዊ ሙስና በሚፈጽመው የምዕራብ አውስትራሊያው ላቦር ፓርቲ ላይ ዘመቻ ጀምሬያለሁ"ሲል አውሴ የሚል ፊርማ ባረፈበት የማህበራዊ ሚዲያ ጽሁፍ ወይም ፖስት ገልጿል።
"ሌበርን አስወግዱ። ድሪል ቤቢ ድሪል" በማለት የአሜሪካ ፕሬዝደንት ትራምፕ ነዳጅ ዘይትና ጋዝ አሜሪካ ውስጥ እንዲወጣ ያቀረቡትን እቅድ የሚያስተጋባ የሚመስል ጽሁፍ በሁለተኛው የኤክስ ፖስታቸው አጋርተዋል።
ፖለቲከኛው ከምዕራብ አውስትራሊያ የስሙን መቀየር ህጋዊት የሚያረጋግጥ ምስል ለጥፏል።
"ቀኝ ዘመሞችን በማወገዝ እንደትራምፕ መሆን እፈልጋለሁ" ሲል መናገሩን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
የምዕራብ አውስትራሊያ ገዥና የግዛቷ የሌበር ፓርቲ መሪ ሮገር ኩክ "ይህ ትኩረት ፍለጋ ነው" ሲሉ አጣጥለውታል።
ፖለቲከኛው "ከዚህ በላይ ምን ያህል የሞራል ዝቅታ ውስጥ እንደሚደርስ አላውቅም" ብለዋል ኩክ።