ሳምሰንግ ያስተዋወቀው አዲሱ S25 ሞባይል ስልክ ምን የተለየ ነገር አለው?
ሳምሰንግ ኩባንያ ኤአይ የተገጠመላቸው ሶስት ሞባይል ምርቶችን ይፋ አድርጓል

አዲሶቹ ስልኮች ከዚህ በፊት ያልነበሩ አዳዲስ አገልግሎቶችን ለተጠቃሚዎች እንዲሰጡ ተደርገው መሰራታቸው ተገልጿል
ሳምሰንግ ያስተዋወቀው አዲሱ S25 ሞባይል ስልክ ምን የተለየ ነገር አለው?
በዓለማችን ካሉ ምርጥ የቴክኖሎጂ እና ኤሌክትሮኒክስ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው ሳምሰንግ ኤአይ ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸው የስልክ ቀፎዎችን ይፋ አድርጓል፡፡
ጋላክሲ ኤስ25 የሰኘው ይህ አዲስ ስልክ ከጎግሉ ጀሚኒ ከተሰኘው ሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር በመቀናጀት መሰራቱ ተገልጿል፡፡
አሁን ላይ የኤሌክትሮኒክስ ኩባንያዎች ከኤአይ ቴክኖሎጂ ጋር ተስማሚ ሆነው እየተሰሩ ሲሆን መሰረቱን ደቡብ ኮሪያ ደረገው ሳምሰንግ ኩባንያም ይህን ውድድር ተቀላቅሏል፡፡
ኤ25 አልትራ፣ ጋላክሲ ኤስ25 እና ኤስ25 የተሰኙ ሞዴሎችን ለገበያ ያቀረበው ሳምሰንግ ተጠቃሚዎች አዲስ እና ቀላል አገልግሎቶችን እንዲያገኙ የሚያደርጉ ናቸው ተብሏል፡፡
አዲሶቹ ስልኮች በድምጽ አማካኝነት ኢሜይሎችን፣ ስልክ ቁጥሮችን፣ ፊልሞችን እና ሌሎች አገልግሎቶችን ማግኘት የሚያስችሉም ናቸው፡፡
እንዲሁም በሁካታ እና ረብሻ ውስጥ የተቀረጹ ፊልሞችን፣ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ያለረብሻ ለመመልከት፣ መስማት የሚፈልጉትን ብቻ መርጦ ማሰማት እና መሰል አገልግሎቶችንም መስጠት ይችላሉ ሲል ዩሮ ኒውስ በቴክኖሎጂ አምዱ አስነብቧል፡፡
ኩባንያው ምርቶቹን በአሜሪካዋ ሳንጆሴ የምርት ማዕከሉ ለደንበኞቹ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋወቀ ሲሆን ቀስ በቀስ በመላው ዓለም ላሉ ደንበኞቹ ለገበያ እንደሚያቀርብም አስታውቋል፡፡
ቅንጡ ነው የተባለው አልትራ ሳምሰንግ 25 የተሰኘው የስልክ ሞዴል በ1 ሺህ 300 ዶላር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ እንደ አገልግሎታቸው ዋጋቸውም ይቀንሳል ተብሏል፡፡